በሰኔ 16ቱ ሽብር ወንጀል የተከሰሱ አምስት ግለሰቦች የጥፋተኝነት ፍርድ ተላለፈባቸው

0
72


ሰኔ 16 ቀን 2010 ዓ.ም ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ድጋፍ መስቀል አደባባይ ላይ በተጠራው ሰልፍ ላይ ቦምብ በመወርወር የሰው ሕይወት በመቅጠፍ እና ንብረት በማጥፋት ጨምሮ በሽብር ወንጀል የተከሰሱት አምስት ግለሰቦች የጥፋተኝነት ፍርድ ተላለፈባቸው።

የጥፋተኝነት ፍርድ የተላለፈባቸው ጌጡ ግርማ፣ ብርሃኑ ጃፋር፣ ጥላሁን ጌታቸው፣ ባሕሩ ቶላ እና ደሳለኝ ተስፋዬ የተባሉ ግለሰቦች ናቸው።

አምስቱም ግለሰቦች በጋራ ስምምነት በወቅቱ በመስቀል አደባባይ ቦምብ በመወርወር የሁለት ሰዎች ሕይወት እንዲጠፋ እና ሌሎች 163 ሰዎች ላይ ደግሞ አካል ጉዳት እንዲደርስባቸው ማድረግን ጨምሮ ሌሎች ዝርዝር ወንጀሎችን ጠቅሶ ዐቃቤ ሕግ በዋና ድርጊት ፈጻሚነት እና ተባባሪነት ከሷቸዋል።

ፍርድ ቤቱ ከዚህ ቀደም የዐቃቤ ሕግ ምስክር ሰምቶ ተከሳሾችም የመከላከያ ምስክር አቅርበዋል፤ የሁለቱን ወገን ክርክር የመረመረው የከፍተኛ ፍርድ ቤት አንደኛ የፀረ ሽብር እና ሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮች ችሎት በዛሬው ዕለት ሁሉም ተከሳሾች ላይ የጥፋተኝነት ፍርድ አስተላልፎባቸዋል።

የቅጣት ውሳኔ ለመስጠትም ለጥቅምት 17 ቀን 2013 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል::

አዉሎ ሚዲያ ነሀሴ 23/2012 ዓ.ም

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ