ህፃናትን በተመለከተ የወጣው አዲሱ የኮሮና ቫይረስ ጥናት

0
96

ከዚህ ቀደም የተሠሩ ጥናቶች፤ በርካታ ልጆች መጠነኛ የበሽታውን ምልክት እንደሚያሳዩ ወይም እስከነጭራሹ ምልክት እንደማይታይባቸው የሚጠቁሙ ናቸው።
እነዚህ ግኝቶች ልጆች ምን ያህል በሽታውን ያሰራጫሉ? ለሚለውና እስካሁን ግልጽ ምላሽ ላልተገኘለት ጉዳይ ፍንጭ ይሰጣሉ።


ለወራት እንቅስቃሴ አቁመው በነበሩ አገሮች ትምህርት ቤቶች እየተከፈቱ ነው። አካላዊ ርቀትና ንጽህናን መጠበቅ መዘንጋት እንደሌለበትም ተመራማሪዎች ይናገራሉ።
ኮቪድ-19 እና ልጆችን በተመለከተ ሦስት ዋና ጥያቄዎች እንዳሉ የሚናገሩት የሮያል ኮሌጅ ፕሮፌሰር ራሰል ቪነር ናቸው። የሚከተሉት ጥያቄዎቻቸው ናቸው፦

ልጆች በቫይረሱ እንደሚያዙ በጥናቱ ተረጋግጧል። ፕ/ር ራሰል እንደሚሉት፤ ከፀረ እንግዳ አካላት (አንቲቦዲ) ምርመራ በተገኘ መረጃ መሠረት በተለይም ከ12 ዓመት በታች ያሉ ልጆች ከአዋቂዎች ባነሰ ለቫይረሱ ይጋለጣሉ።

ልጆች በቫይረሱ ከተያዙ የአዋቂዎች ያህል እንደማይታመሙም ሳይንቲስቶች እርግጠኛ ናቸው። እንዲያውም በርካታ ልጆች የበሽታውን ምልክት አያሳዩም።
እምብዛም መልስ ያልተገኘለት ጥያቄ ልጆች በሽታውን ወደ ሌላ ሰው ያስተላልፋሉ የሚለው ነው። የደቡብ ኮርያው ጥናትም እዚህ ላይ ያተኮረ ነው።

ጥናቱ የተሠራው 91 ልጆች ላይ ነው። መጠነኛ ወይም ምንም ምልክት የማያሳዩ ልጆች እስከ ሦስት ሳምንት ድረስ ቫይረሱ እንደሚቆይ ከናሙና መረዳት ተችሏል።
አፍንጫቸው ላይ የቫይረሱ ምልክት መገኘቱ፤ ልጆች በሽታውን ወደ ሌላ ሰው ማስተላልፍ እንደሚችሉ እንደሚጠቁም የጥናቱ ጸሐፊዎች አስረድተዋል።


ደቡብ ኮርያ በምታካሂደው ምርመራና በሽታው ካለባቸው ሰዎች ጋር ንክኪ ያላቸውን ሰዎች በምትለይበት ሂደት አማካይነት፤ የበሽታውን ምልክት የማያሳዩ ሰዎች ሳይቀሩ ይገኛሉ። ህሙማን ከተለዩ በኋላ ከቫይረሱ ነፃ እስኪሆኑ በተደጋጋሚ ተመርምረዋል።

ጥናቱ ልጆች ቫይረሱን እንደሚሸከሙ፣ ወደ ሌሎች ሰዎች ሊያስተላልፉ እንደሚችሉም ጠቁሟል። ሆኖም ግን ለሁሉም ጥያቄዎች መልስ አልሰጠም። ልጆች አፍንጫ ላይ ቫይረሱ ተገኝቷል ማለት የአዋቂዎች ያህል ቫይረሱን ያስተላልፋሉ ማለት አይደለም።

በሕፃናት ሕክምና ክፍል የሚሠሩት ዶ/ር ሮበርታ ዲባሲ ልጆች ቫይረሱን ሊያስተላልፉ አይችሉም ማለት እንደማይቻል ያስረዳሉ። የቫይረሱ ዘረ መል ከመተንፈሻ አካላት በሚወሰድ ናሙና ላይ መገኘቱ በሽታውን ከማስተላለፍ ጋር የግድ እንደማይተሳሰር የሚናገሩት ደግሞ የሊቨርፑል ዩኒቨርስቲ ፕ/ር ካሉም ሰምፕል ናቸው።

የጥናቱ ድምዳሜ እንደሚለው ከሆነ ልጆችም ይሁን አዋቂዎች መጠነኛ ወይም ምንም አይነት ምልክት ካላሳዩ በሽታውን የማስተላለፍ እድላቸው አናሳ መሆኑን ጥናቶች ያሳያሉ። የማያስሉ ወይም የማያስነጥሱ ሰዎች ቫይረሱን ወደ አየር እምብዛም አይለቁም። ሆኖም ግን ምልክት የማያሳዩ ሰዎች በሽታውን አያሰራጩም ማለት አይደለም።


ዶክተሩ እንደሚሉት፤ አብዛኞቹ ልጆች በተወሰነ ደረጃ ወይም ሊታይ በማይችል ሁኔታ ነው በቫይረሱ ሊያዙ የሚችሉት። በማኅበረሰቡ ውስጥ ቫይረሱን ሊያሰራጩ ግን ይችላሉ።


አዉሎ ሚዲያ ነሀሴ 23/2012 ዓ.ም

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ