አብን የፌደራል መንግስት ህግ እና ስርአት እንዲያስከብር ድጋሜ ጠየቅ

0
131

አብን ይህን ያለው ካሳለፍነው ወር ጀምሮ አሁንም ድረስ በዘለቀው ሁከትና ብጥብጥ በኦሮሚያ መከሰቱን እና ዘር ተኮር ጥቃት እየደረሰ ነው በሚል ባወጣው መግለጫው ነው።


አብን በመግለጫው በቅርቡ በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች የተፈፀመው «የዘር ማጥፋት ወንጀል» እንደሆነ በመግለፅ በጥፋቱ የተሳተፉ፣ ሕዝቡን ከጥቃት የመከላከል ኃላፊነታቸውን ያልተወጡ የመንግስት አመራሮችም በጉድለታቸው ልክ በሕግ ተጠያቂ እንዲሆኑ እና ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖችን የመልሶ ማቋቋም ስራ እንዲሰራ ጥሪ ማቅረቡ ይታወሳል ያለ ሲሆን ፤ አብን ጥቃቱ መፈፀም ከጀመረበት ዕለት አንስቶ የነቃ ክትትል በማድረግ በርካታ ወገናዊ ኃላፊነቱን ሲወጣ ቆይቷልም ብሏል ።

ከዚሁ ጋር ተያይዞ በኦሮሚያ ክልል በሆሮጉድሩ ዞን ጃርኔጋ ወረዳ ነሽ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከነሐሴ 12 ቀን 2012 ዓ.ም ጀመሮ በተፈፀሙ ዘር-ተኮር ጥቃቶች ከአስራ አምስት(15) በላይ አማራዎች በአሰቃቂ ሁኔታ የተገደሉ ሲሆን በርካቶችም መፈናቀላቸውን አብን አረጋግጧል ብሏል። ይህን ዘር ተኮር ጥቃት ሲደርስ ህዝቡን ከጥቃት ማትረፍ ያልቻሉት የመንግስት አካላት መጥየቅ አለባቸው ብሎ አብን ያምናል።

አብን ባሳለፍናቸው ሳምንታት ስለታሰሩት የአስራት ቴቪ ጋዜጤኞች አስመልክቶም ለመንግስት ማሳሰብያ የሰጠ ሲሆን፤ ለጥፋተኞች የፖለቲካ ሚዛን መጠበቂያነት ሲባል ነው የታሰሩትም ሲል ፖለቲካ ፓርቲው ገልፅዋል። የአስራት ቴሌቪዥን ወሳኝ ለሆኑ የአማራ ሕዝብ ጉዳዬች የሚዲያ ሽፋን በመስጠት ጉልህ ድርሻ ሲወጣ ቆይቷልም ብሏል።
እነዚህ እና መሰል የህግ ጥሰት የፈፅሙ ወንጀለኞች መንግስት እንደሚናገረው በተግባር ህግ እንዲያስከብር አብን አጥብቆ መንግስትን ጠይቋል።


አዉሎ ሚዲያ ነሀሴ 22/2012 ዓ.ም

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ