184 ባለስልጣናት ሊከሰሱ ነው !

0
119

የፌደራል ስነምግባርና ጸረ-ሙስና ኮሚሽን ሀብታቸውን ለማስመዝገብ ፍቃደኛ ያልሆኑ 184 ባለስልጣናት በወንጀል እንዲከሰሱ ስም ዝርዝራቸውን ለፌደራል ፖሊስ መስጠቱን አስታውቋል ፡፡
ሀብትና ንብረታቸውን ማስመዝገብ ያለባቸው የመንግስት ሹመኞች በተደጋጋሚ እንዲያስመዘግቡ ቢጠየቁም ለማስመዝገብ ፍቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል ብሏል ኮሚሽኑ፡፡

ኮሚሽኑ ባለስልጣናቱ ሀብታቸውን እንዲያስቀምጡ ያስቀመጠው ቀነገድብ ባለፈው ሀምሌ 30 ለሁለተኛ ጊዜ በማለፉ ምክንያት ተጠያቂ እንዲሆኑ ማድርጉን ገልጿል፡፡

በቀነገደቡ ማስመዝገብ ያልቻሉ 184 የፌደራና የአዲስ አባባ መገኘታቸውንና እነሱም በህግ ይጠየቃሉ ብሏል ኮሚሽኑ፡፡
ኮሚሽኑ የባለስልጣናቱን ስም ዝርዝር ግን ይፋ አላደረገም፡፡ በ2002 ዓ.ም በተወካዮች ምክርቤት በወጣው አዋጅ መሰረት ባለስልጣናት ሀብታቸውን እንዲያስመዘግቡ ያስገድዳል፡፡

አዉሎ ሚዲያ ነሀሴ 21/2012 ዓ.ም

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ