ፖል ፖግባ በኮሮና ቫይረስ ተያዘ

0
156

ፖል ፖግባ በኮሮና ቫይረስ ተያዘየማንችስተር ዩናይትዱ አማካይ ፖል ፖግባ ኮሮና ቫይረስ እንደተገኘበት የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ዲዲየር ዴሾ ገልጸዋል፡፡ዴይሊ ሜይል እንደዘገበው ፖግባ ከጥቂት ቀናት በፊት ለንደን በሚገኝ አንድ ሬስቶራንት ከነፍሰጡር ባለቤቱ ጋር ተገኝቶ ነበር፡፡

የ27 ዓመቱ ፖግባ በቀጣዩ ወር በአውሮፓ ሀገራት ዉድድር ለሀገሩ ብሔራዊ ቡድን ተሰልፎ እንዲጫወት ተመርጦ የነበረ ቢሆንም በቫይረሱ ምክንያት በሌላ ተጫዋች ተተክቷል፡፡ፖግባ ለቀጣዮቹ 14 ቀናት ራሱን አግልሎ እንደሚያቆይም በዘገባው ተገልጿል፡፡

ተጫዋቹ ከበሽታው አገግሞ እንደ አውሮፓውያኑ በቀጣዩ መስከረም 19 ማንችስተር ዩናይትድ ከክሪስታል ፓላስ ጋር ለሚያደርገው የፕሪሚየር ሊግ የመክፈቻ ጨዋታ ሊደርስ ይችላል ተብሏል፡፡ ዴይሊ ሜይል ዋቢ አድርጎ አል ዐይን ዘግቦታል።

አዉሎ ሚዲያ ነሀሴ 21/2012 ዓ.ም

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ