በርካታ ሕጻናት ወሳኝ የሆኑ ክትባቶችን አለመውሰዳቸውን የተባበሩት መንግሥታት ገለፀ

0
108

ባለፈው ዓመት በመላው ዓለም 14 ሚሊዮን ሕፃናት በቀላሉ መከላከል ከሚቻሉ ሕመሞች ለመጠበቅ የሚያስችለውን ክትባት አለመከተባቸውን የዓለም ጤና ድርጅት እና ዩኒሴፍ በጋራ በሰጡት መግለጫ አስታወቁ።

በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የወጣው ሪፖርት ጨምሮ እንዳስታወቀው በዚህ ዓመትም በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ክትባቶች በመቋረጣቸው ይህ ቁጥር በእጥፍ ይጨምራል።

ድርጅቶቹ አክለው እንደገለፁት ከ30 ዓመታት ወዲህ በኮሮናቫይረስ ምከንያት በርካታ ቁጥር ያላቸው ሕጻናት ህይወት አድን የሆኑ ክትባቶች አለመከተባቸውን በመጥቀስ አስጠነቅቀዋል።

ከእነዚህ ሕጻናት መካከል ግማሽ ያህሉ የሚገኙት ግጭት በሚያጠቃቸው የአፍሪካ አገራት መሆኑን ተገልጿል። ዘገባው የቢቢሲ ነው

አዉሎ ሚዲያ ሐምሌ 09/2012 ዓ.ም

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ