በቀን 2 ሚሊየን ዳቦ ያመርታል የተባለው የሸገር ዳቦ ፋብሪካ ተመረቀ

0
141

የሸገር ዳቦ ፋብሪካ ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድና ኢ/ር ታከለ ኡማ በተገኙበት ተመርቆ በይፋ ስራውን ጀምሯል።

ዳቦ ፋብሪካው በቀን 2 ሚሊየን ዳቦ የሚያመርት ሲሆን ለማከፋፈያ የሚውሉ ተሽከርካሪዎችም ተዘጋጅተዋል።

ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን ለመቻል የምታደርገውን ጥረት ለማሳካት በተለያዩ አካባቢዎች ሰፋፊ የስንዴ እርሻዎች መጀመራቸውን እና የተሻለ ምርት ለመሰብሰብ የሚያስችል ልምድም መቀሰሙን የገለጹት ዶ/ር ዐቢይ፣ “ዓላማችን በጥቂት ዓመታት ውስጥ ስንዴን ከውጭ ማስገባት ማቆም ነው” ሲሉ በምረቃው ሥነ ሥርዓት ላይ ተናግረዋል።

“ኢትዮጵያ አሁን ያለችበት ሁኔታ ለወደፊቷ ዕድል ይሆናታል እንጂ እንቅፋት አይሆንባትም፤ ሁሉም ተባብሮ ከሠራ የዛሬ 10 ዓመት የምግብ ጉዳይ ዋና አጀንዳ ያልሆነባት ኢትዮጵያን መገንባት እንችላለን” ሲሉም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

የፋብሪካው ግንባታ በ9 ወራት ውስጥ የተጠናቀቀ ሲሆን ዳቦዎችን በተመጣጣኝ ዋጋ ለህብረተሰቡ የሚያቀርብ ይሆናል።

400 የሚሆኑ የአንበሳ አውቶብሶችም እድሳት ተደርጎላቸው ለመሸጫነት እንዲውሉ በየአካባቢው ተዘጋጅተዋል።

ዳቦዎችን ለተጠቃሚዎች እንዲያደርሱ በየአካባቢው ወጣቶች መደራጀታቸውንም የአዲስ አበባ ከንቲባ ጽ/ቤት አስታውቋል።

አዉሎ ሚዲያ ሰኔ 18/2012 ዓ.ም

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ