የኮሮናቫይረስ እንዳለባቸው ተረጋግጦ ሲፈለጉ ከነበሩት አሽከርካሪዎች መካከል 15 መገኘታቸውን ጤና መምሪያው አስታወቀ

0
97

16 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተጠርጥረው ሲፈለጉ እንደነበር በማለዳ ዜናችን ወደ እናንተ ማድረሳችን ይታወሳል።ከነዚህ 15ቱ መገኘታቸው ደግሞ የሰሜን ሸዋ ዞን ጤና መምርያ ለአ.ብ.መ.ድ አስታውቋል።

በሰሜን ሸዋ ዞን22 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው መረጋገጡን የዞኑ ጤና መምሪያ ትናንት መግለጹ ይታወሳል፡፡ በ79 ሰዎች ላይ ምርመራ ተደርጎ ነበር 22 ሰዎች ቫይረሱ የተገኘባቸው፡፡ ከ79 ተመርማሪዎች 36 አሽርካሪዎች እንደነበሩና ከእነዚህ መካከል 16 የኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸውም ዘግበን ነበር፡፡

ቫይረሱ ከተገኘባቸው 22 ሰዎች መካከል 16ቱ አሽከርካሪዎች እየተፈለጉ እንደሚገኙ የዞኑ ጤና መምሪያ ለአብመድ ገልጾ ነበር፡፡

አሁን በደረሰን መረጃ መሠረት ደግሞ 15 አሽከርካሪዎች ተገኝተዋል፤ ከእነዚህ ውስጥ አስራ ሁለቱ ወደ ደብረ ብርሃን ለይቶ ማከሚያ ማዕከል ተወስደዋል፡፡ ሦስቱ ደግሞ አዲስ አበባ ወደ ሚገኝ ለይቶ ማከሚያ ማዕከል እንዲገቡ ሊደረግ መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡ አንድ አሽከርካሪ ተንቀሳቃሽ ስልኩ ጥሪ ባለመቀበሉ እስካሁን እንዳልተገኘና ፍለጋው መቀጠሉንም ጤና መምሪያው አስታውቋል፡፡

በአማራ ክልል ትናንት ሰኔ 8/2012 ዓ.ም ይፋ የተደረገ መረጃ እንደሚያሳየው ከ624 የላቦራቶሪ ምርመራ በ33 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቷል፡፡

በክልሉ እስከ ትናንት ሰኔ 8/2012 ዓ.ም ድረስ ለ5 ሺህ 590 ሰዎች የናሙና ምርመራ ተደርጎ በ231 ሰዎች ቫይረሱ መገኘቱን የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ማሳወቁ ይታወሳል፡፡ በክልሉ አጠቃላይ ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥርም 44 መድረሱን ይታወሳል፡፡

አዉሎ ሚዲያ ሰኔ 09/2012 ዓ.ም

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ