በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ተጨማሪ 179 ሰዎች ሲገኙ የ2 ሰዎች ህይወት አለፈ

0
85

ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ 4845 የላቦራቶሪ ምርመራ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ተጨማሪ 179 ሰዎች ተገኝተዋል። አዲስ የተገኙትን ጨምሮ ባጠቃላይ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 3345 ደርሷል፡፡ ትናንት ቫይረሱ የተገኘባቸው ግለሰቦች የእድሜ ክልላቸው ከ 2 ወር እስከ 80 ዓመት ሲሆን 116 ወንዶች እና 63 ሴቶች ናቸው፡፡

በዜግነት 176 ሰዎች ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ 3ቱ የዉጭ ዜጎች መሆናቸውን የገለጹት የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ 111 ሰዎች ከአዲስ አበባ፣ 9 ከትግራይ ፣ 15 ከኦሮሚያ ፣ 23 ከአማራ ፣ 11 ከአፋር ፣ 5 ከሶማሌ ፣ 2 ከደቡብ ፣ 2 ከድሬ ዳዋ እና 1 ከሀረሪ እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡

በአስከሬን ምርመራ ተጨማሪ 2 ግለሰቦች ደግሞ ህይወታቸው በቫይረሱ ማለፉ የተረጋገጠ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 57 ደርሷል፡፡በሌላ በኩል ትናንት 50 ሰዎች ያገገሙ ሲሆን አጠቃላይ ያገገሙት ቁጥርም 545 ደርሷል፡፡

አዉሎ ሚዲያ ሰኔ 07/2012 ዓ.ም

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ