ሱዳን የሶስትዮሽ ድርድር የስምምነት ሰነድ እንድትቀርጽ ሃላፊነት ተሰጣት

0
83

ሱዳን የኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብጽ የሶስትዮሽ ድርድር አቀራራቢ የስምምነት ሰነድ እንድታዘጋጅ ኃላፊነት እንደተሰጣት የአገሪቱ መንግስት አስታወቀ። በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የውሃ አሞላልና አለቃቀቅ ዙሪያ ከቀናት በፊት የተጀመረው የሶስትዮሸ ድርድር ዛሬም እንደቀጠለ ነው።

በእንጥልጥል ላይ በሚገኘው የታላቁ ሕዳሴ ግድብ የሶስትዮሽ ድርድር ሱዳን ሁሉንም ወገን ሊያስማማ የሚችል ሰነድ እንድታዘጋጅ ተልዕኮ እንደተሰጣት የአገሪቷን የመስኖ ሚኒስቴርን መረጃ ጠቅሶ ሱዳን ትሪቡን ዘግቧል።አገራቱ የመጀመያሪው ዙር አሞላልና የውሃ አለቃቅ ዙሪያ በተፈጠረውል ልዩነት ስምምነት ላይ ለመድረስ ላለፉት አራት ቀናት በቪዲዮ ኮንፈረንስ እየተወያዩ ነው።

የዛሬው ውይይት አጀንዳም በመደበኛ ዝናባማ ወራት፣ በአጭር ወራት እንዲሁም በተራመዘ የድርቅ ዓመታት ስለሚደረገው የግድቡ ውሃ አሞላልና አለቃቀቅ ቴክኒካል ጉዳዮች መሆኑን ዘገባው ጠቅሷል።በውይይቱ የሚነሱ ሃሳቦችን መሰረት በማድረግ ሶስቱንም አገሮች የሚያስማማ ሠነድ እንድታዘጋጅ ሁሉም ወገኖች ከስምምነት ላይ መድረሳቸውን ነው ሱዳን ትሪቡን የዘገበው።

በነገው የድርድር ውሎም ሱዳን በምታዘጋጀው አዲስ የስምምነት ረቂቅ ሰነድ፣ የድርድር ሂደት ግምገማ እንዲሁም በቀጣይ እርምጃዎች ዙሪያ እንደሚሆን ገልጿል።ውይይቱ ትናንት ሰኔ 6 ቀን 2012 ዓ.ም ይጠናቀቃል ተብሎ ቀነ ቀጠሮ ቢያዝለትም ዛሬም ቀጥሏል።ውይይቱ ከውስን ዝርዝር ጉዳዮች በስቀር አብዛኛው ነጥቦች ላይ ተደራዳሪዎች በመስማማታቸ በስምምነቱ ሕጋዊ ጉዳዮች ላይ ጭምር መወያየታቸውን ጠቅሷል።

በውሃ አሞላል ወቅት በሚለቀቀው የውሃ መጠን ረገድ በዋናነት ልዩነቱ በኢትዮጵያና በግብጽ መካከል እንደሆነ ያመለከተው ዘገባው፤ ሱዳን ሁለቱ ግድቦቿ በማይጎዱበት መልኩ አሞላሉና አለቃቀቁ እንዲከናወን የትብብር ስልት እንደምትሻ ገልጻለች ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

አዉሎ ሚዲያ ሰኔ 7/2012 ዓ.ም

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ