የህዳሴ ግድብን ከጀመርን ጀምሮ እንደ አሁኑ የዲፕሎማሲው ስራ ጠንካራ ፈተና ገጥሞን አያውቅም –ጠ/ሚ አብይ አብይ አህመድ

0
128

ጠ/ሚንስትሩ የታላቁ ህዳሴ ግድብን አስመልክተው በሰጡት ማብራርያ ነው ይህን ያሉት። አክለውም ግድቡ በተያዘለት የፕሮጀክት ጊዜ ባለመጠናቀቁና በመቆየቱ ምክንያት ኢትዮጵያ በእያንዳንዱ አመት አንድ ቢሊዮን ብር አጥታላች፤ በስድስት አመት ስድስት ቢሊዮን ብር አጥታለች፤ ይሀ ዶላርና ዩሮውን ሳይጨምር ነው ያሉ ሲሆን።

የህዳሴ ግድብን ከጀመርን ጀምሮ እንደአሁኑ የዲፕሎማሲው ስራ ጠንካራ ፈተና ገጥሞን አያውቅም ሲሉም ተናግረዋል። የተለያዩ የሀገሪትዋ የፖለቲካ ሙሁራን እና የፖለቲካ ፓርቲ ሀላፊዎች አባይ ግድብን አስመልክቶ መንግስት ሲያካሂድ የነበረውን ድርድር ሲውቅሱ እንደነበረ የሚታውስ ሆኖ ግድቡን ከጥፋት ታድገነዋል፤ ስራው አስተማማሽ ሆኖ ስለቀጠለ በዘንድሮው ክረምት 4.9 ቢሊዮን ሜትርክ ኪዩብ ውሃ እንይዛላን ሲሉ ጠ/ሚ ተናግረዋል።

ጨምረውም ግድቡን በመስራታችን የምንጎዳው አገር የለም፤ እያልን ያለነው መብራትና ውሃ የማያገኙ ዜጎቻችን ይጠቀሙ ነው፤ ይሄ ደግሞ ከማንም የማንለምነው መሰረታዊ መብታችን ነው በለዋል።

ጣና ሐይቅ አስመልከተው ብሰጡት ማብራርያ በሀይቁ የሚገኘውን የእንቦጭ አረም የማስወገድ ሥራው በማሽን እንዲሁም የሰው ኃይል በመጠቀም መከናወኑን ቀጥሏል፡፡ነገር ግን፣ ዘላቂ መፍትሔ አይደለም፡፡የችግሩን ዋነኛ መንስኤ በማስወገድ የአካባቢ ጥበቃ ሥራ መሥራትን ይጠይቃል ብለዋል፡፡

መንግሥት በዚህ ጉዳይ ላይ ትኩረት ያደረገ ሲሆን፣ተጨማሪ ማሽኖችም በመገዛት ላይ ናቸው ያሉ ሲሉም አክለዋል።

አዉሎ ሚዲያ ሰኔ 01/2012 ዓ.ም

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ