ወይዘሮ ኬሪያ ኢብራሒም በፍቃዳቸው ስልጣናቸውን ለቀቁ

0
158

የኢፌድሪ ፌዴሬሽን ምክር ቤት ኣፈ ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ ኬርያ ኢብራሂም በገዛ ፍቃዳቸው ሰልጣናቸው ለቀቁ።

ባለፉት በርካታ አመታት በፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩት ወይዘሮ ኬርያ በፈቃዳቸው ስልጣን ለቀቁ በማለት ትግራይ ማስ ሚዲያ ኤጀንሲ ዘግቧል።

በቅርቡ የምርጫ መራዘምን ተከትሎ የህገ-መንግስት ትርጉም ለመስጠት የተጀመረው ሒደት ወደ ፌዴሬሽን ምክር ቤት የተመራው ባለፈው ሳምንት ነው።

ይህንን የህገ መንግስት ትርጓሜ ሒደት ህወሓት እየተቃወመው የነበረ ሲሆን የህወሓት አባል የሆኑትና የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ኬሪያ ስልጣናቸውን ሕገ መንግስት ከሚጥስ እና ከአምባገነን ቡድን ጋር አብሮ መስራት ፍቃደኛ አይደለሁም ሲሉም ተናግረዋልሲል የዘገበው ትግራይ ቴሌቪዥን ነው።
ሙሉውን መግለጫ ከ ሰአታት በኋላ ትሰጣለች ሲልም ቴሌቪዥን ጣብያው ዘግቧል።

በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ መረጃዎችን የምናደርስ ይሆናል።

አዉሎ ሚዲያ ሰኔ 01/2012 ዓ.ም

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ