መንግስት ለ2013ዓ.ም 476,012,952,445 ብር ረቂቅ በጀት አቀረበ

0
132

የሚኒስትሮች ምክርቤት በዛሬው እለት ባካሄደው ስብሰባ የ2013 ዓ.ም የመንግስት ረቂቅ በጀት 476 ቢሊዮን ብር እንዲሆን መወሰኑን የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት አስታውቋል፡፡

በሚስትሮች ምክርቤት የቀረበው ረቂቅ በጀት ለፌደራል መንግስት መደበኛ ወጭ፤ለካፒታል ወጭ፣ ለክልሎች በሚሰጥ ድጋፍና ለዘላቂ ልማት ግቦች ማስፈጸሚያ ለማዋል እንደሚከፋፈል ተገልጿል፡፡ ከበጀት ጉዳይ በተጨማሪ ምክርቤቱ በኮሮና ቫይረስ ስርጭት ጉዳይና አንበጣን ለመከላከል ለሚያስችል ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ የሚውል የብድር ስምምነት አጽድቋል፡፡

አዉሎ ሚዲያ ግንቦት 29/2012 ዓ.ም

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ