በኢትዮጵያ 150 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው የ1 ሰው ህይወትም አልፏል

0
86

በኢትዮጵያ 150 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው የ1 ሰው ህይወት አልፏል ። ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 5 ሺህ 141 የላብራቶሪ ምርመራ 150 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች 1 ሺህ 637 መድረሱን የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ባወጡት እለታዊ ሪፖርት ገልፀዋል።በሌላ መልኩ 4 ሰዎች ያገገሙ ሲሆን፥ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 250 ደርሷል።

በሌላ ዜና የኮሮና ቫይረስ በምርመራ ተገኝቶበት በኤካ ኮተቤ ሆስፒታል ህክምና ሲደርግለት የነበረ፣ ከዚህ ቀደም ተጓዳኝ ህመም ያለበት እና በፅኑ ህክምና ላይ የነበረ የ30 ዓመት ኢትዮጵያዊ በትላንትናው ዕለት ህይወቱ ሊያልፍ ችሏል።

በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ የተገኘባቸው እና ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር አስራ ስምንት (18) ደርሷል፤የጤና ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በህልፈተ ህይወታቸው የተሰማቸውን ሀዘን እየገለጹ ለቤተሰቦቹ መፅናናትን ተመኝተዋል።

አዉሎ ሚዲያ ግንቦት 27/2012 ዓ.ም

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ