በቀጣይ ሣምንት ለሕዳሴው ግድብ ውሃ ሙሌት የሚሆን 1 ሺህ ሄክታር መሬት ምንጣሮ ይጀመራል

0
84

ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ውሃ ሙሌት የሚሆን አንድ ሺ ሄክታር መሬት የምንጣሮ ስራ በመጪው ሣምንት እንደሚጀመር የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አስታወቀ።

ለምንጣሮ ስራው 300 ወጣቶች በጥቃቅንና አነስተኛ ማኅበራት መደራጀታቸውም ታውቋል።

ኢዜአ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ አሻድሊ ሀሰንና የሕዳሴው ግድብ ግንባታ ፕሮጀክት ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮ ን በስልክ አነጋግሯል።

አቶ አሻድሊ እንደገለጹት ቀደም ሲል በብረታብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን /ሜቴክ/ ተጀምሮ የነበረው የደን ምንጣሮ ውጤታማ አልነበረም።

ከአገራዊ ለውጡ በኋላ ትላልቅ ፕሮጀክቶችን በፍጥነትና በጥራት ለማጠናቀቅ በትኩረት እየተሰራ ስለ መሆኑ ገልጸው የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታን በማሳያነት ጠቅሰዋል።

ይህ በንዲህ እንዳለም የኢ/ያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላ ም/ቤት የአባይ ግድብን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥትዋል፡፡ ጠ/ምቤቱም በመግለጫው በባህልና በሀይማኖት ጥብቅ ቁርኝት ያላቸው ግብፅና ኢ/ያ የአባ ውሀ ብቸኛው ተጠቃሚ እኔ ነኝ በሚለው የግብፅ አቋም ምክንያት ዛሬ ወደ ደረሰበት ደረጃ ይወርዳል የሚል እምነት አልነበረንም ብሏል፡፡ በመግለጫው አክሎም የኢ/ያ ህዝብ በቋንቋ ፣በዘር፣ በሀይማኖት ሳይከፋፈል እስከ መጨረሻ ድረስ ጥረቱን እንዲቀጥል አሳስቧል፡፡

አዉሎ ሚዲያ ግንቦት 27/2012 ዓ.ም

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ