ተጨማሪ 87 ሰዎች ኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው፤ የሁለት ሰዎች ህይወት አለፈ

0
104

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገ 3932 የላቦራቶሪ ምርመራ ተጨማሪ 87 ሰዎች ኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ።

በዚህም በሀገሪቱ እስካሁን ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች 1344 ደርሷል።።

ተጨማሪ 14 ሰዎች ያገገሙ ሲሆን እስካሁን 231 ሰዎች ከበሽታው ማገገማቸውን ሚኒስትሯ ገልጸዋል።

ሚኒስትሯ እንደገለፁት ቫይረሱ እንደተገኘባቸው የተረጋገጠው እድሜያቸው ከ10 እስከ 70 ዓመት ነው፡፡

በምርመራ ቫይረሱ እንዳለባቸው ከተረጋገጠው 59 ወንድና 28 ሴቶች ሲሆኑ ሁሉም ኢትዮጵያውያን ናቸው።

ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች 67 ሰዎች ከአዲስ አበባ ሲሆኑ፣2 ሰዎች ከትግራይ ክልል፤6 ኦሮሚያ ክልል እና 7 ከአማራ ክልል እንዲሁም አንድ ሰው ከሐረሪ እና 4 ሶማሌ ክልል ናቸው፡፡

በዚህም መሰረት ዛሬ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች 28 የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ ያላቸው፣ 18 በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት ያላቸው እንዲሁም 41 ሰዎች ደግሞ የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክም ሆነ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት የሌላቸው መሆናቸውን ዶክተር ሊያ ተናግረዋል፡፡

በዛሬው እለት የሁለት ኢትዮጵያውያን ሕይወት ማለፉም የታወቀ ሲሆን፤ በአጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 14 ደርሷል፡፡

ቫይረሱ ተገኝቶባቸው በለይቶ ህክምና ውስጥ ያሉ ሰዎች 1097 ናቸው።

ስምንት ሰዎች በጽኑ ህክምና ክፍል ክትትል እየተደረገላቸው መሆኑም ታውቋል።

እስካሁን በኢትዮጵያ አጠቃላይ 116 ሺህ 309 የላቦራቶሪ ምርመራ ተከናውኗል።

አዉሎ ሚዲያ ግንቦት 25/2012 ዓ.ም

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ