ጥንታዊ እስራኤላውያን ዕፀ ፋርስን በማጨስ ለአምልኮት ይጠቀሙበት ነበር ተባለ

0
313

ጥንታዊ እስራኤላውያን ዕፀ ፋርስን ማጨስ የአምልኮታቸው አካል አድርገው ያዩት እንደነበር በቅርቡ አንድ የቅሪተ አካል (አርኪዎሎጂ) ጥናት ይፋ አድርጓል።ከ2 ሺህ 700 ዓመታት በፊት የነበረ አራድ የተባለ ምኩራብ ላይ የዕፀ ፋርስ ቅሪቶች መገኘታቸውም ተገልጿል።

ተመራማሪዎቹ በምኩራቡ ውስጥ በሚደረጉ የአምልኮ ስነስርአቶች ላይ ዕፀ ፋርስ ይጨስ የነበረው ለምዕመናኑ የተለየ ስሜት እንዲሰጣቸው ለማድረግ እንደሆነም በጥናታቸው አመላክተዋል። በጥንታዊ አይሁዳውያን አማኞች ዕፀ ፋርስ ሲገኝ የመጀመሪያው እንደሆነ የእስራኤል ሚዲያ ሪፖርት አድርጓል።

በደቡባዊ ቴል አቪቭ፣ ኔጌቭ በረሃ ስለሚገኘው ይህ ምኩራብ መጀመሪያ የታወቀው በጎርጎሳውያኑ 1960ዎቹ ነው።

የቴል አቪቭ ዩኒቨርስቲ የአርኪዎሎጂ መፅሄት እንዳሳተመው ሁለት ከድንጋይ የተሰሩ መሰዊያ/ ማጨሻዎች/ ከአምልኮ ቦታው ጋር ተቀብረው ተገኝተዋል።

የአካባቢው የአየር ንብረት ደረቃማ በመሆኑና በአቀባበሩም የተነሳ ይጨስ የነበረው የእፀ ፋርስ ቅሪት በደህና ሁኔታ ተገኝቷል ተብሏል።

በአንደኛው ማጨሻ ላይ ከእፀ ፋርስ በተጨማሪ እጣንም ተገኝቷል።

በተለያዩ ቅዱሳት መፃህፍት በተደጋጋሚ እጣን ከመጠቀሱ ጋር ተያይዞ እጣን የመገኘቱ ሁኔታ እንዳላስደነቃቸው የእስራኤሉ ጋዜጣ ሃሬትዝ ጥናት አድራጊዎቹን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።

በቴል አቪቭ አራድ ምኩራብ ዕፀ ፋርስ መገኘቱ በተመሳሳይ ሁኔታ በእየሩሳሌም ምኩራቦች ላይም ዕፀ ፋርስን ለአምልኮ ይጠቀሙበት ነበር የሚለውን አመላክቷል።

ለዚህም እንደ ምክንያትነት የተጠቀሰው የአራድ ምኩራብ በደቡባዊው የይሁዳ ስርወ መንግሥት ኮረብታዎች አካል ሲሆን፤ ይህም በመፅሃፍ ቅዱስ ውስጥ በእየሩሳሌም የመጀመሪያው ምኩራብ ተብሎ ከሚጠራው ጋር በመመሳሰሉ ነው።

በእየሩሳሌም የሚገኙ ምኩራቦች ለአርኪዎሎጂስቶች ጥናት ክፍት ያልሆኑ ሲሆን ለጊዜውም በአራድና በተመሳሳይ አምልኮ ቦታዎች ጥናቱ ይቀጥላል ተብሏል።

አዉሎ ሚዲያ ግንቦት 24/2012 ዓ.ም

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ