29ኛው የግንቦት 20 በአል ስናከብር አሁን እንደ ህዝብ ያጋጠመን አዲስ የትግል መድረክ በአንድነት ቆመን በመመከት መሆን አለበት አሉ የትግራይ ክልል ም/ አስተዳደር ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል

0
114

ም/ር መስተዳድሩ 29ኛው የግንቦት 20 በአልን አስመልክተው ባስተላለፉት መልእክት ነው ይህን ያሉት፡፡ ዶ/ር ደብረፅዮን አክለውም 29ኛው የግንቦት 20 በአል ስናከብር የትግራይ ህዝብ የትግል ታሪክ ያሰብን ፣ ያጠፋናቸው ስህተቶች ን ደግመን በማየት እንዲሁም በመፈተሸ ፣ የትግራይ ህዝብ በትግል ታሪኩ ያስመዘገባቸው ድሎችን በማስታወስ ነው ብለዋል፡፡

 ደ/ር ደብረፅዮን ለወጣቶች /ለድጅታል ወያነ ብለው ባስተላለፉት መልእክታቸው በህልውናችን ላይ የተጋረጡት ሴራዎና ተከታታይ ፖለቲካዊና ዲፕሎማሲያዊ ጥቃቶች ደከመኝ ሰለቸኝ ሳትሉ በምታካሂዱት የሴረኞቹ ሴራ በማክሽፍ ፣ የአባቶቻችሁ አደራን በመጠበቅ ለምታደርጉት እንቅስቃሴ እጅጉን ምስጋና ይገባችኋልም ብለዋል፡፡

አዉሎ ሚዲያ ግንቦት 20/2012 ዓ.ም

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ