“ግንቦት 20 ለሶማሌ ክልል ህዝብ ካስገኘለት ጥቅም ይልቅ ጉዳቱ ያመዝናል” አሉ — አቶ ሙስጠፌ ሙሀመድ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር

0
246

ግንቦት 20 ለሶማሌ ክልል ህዝብ በቋንቋው ከመማርና ራስን በራስ ከማስተዳደር መብት ካስገኘለት ጥቅም ይልቅ ከፍተኛ የሆነ የሰብዓዊ መብት ጥሰትና የፀጥታ ችግር በመፍጠር መጥፎ አሻራ ማሳረፉን የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ተናገሩ፡፡

የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ሙሀመድ  ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለፁት፤ በግንቦት 20 በአገር አቀፍ ደረጃ የፌዴራል ሥርዓት ተግባራዊ መደረጉን ተከትሎ የሱማሌ ክልል ህዝብ በቋንቋው የመማር፣ ራስን በራስ የማስተዳደር መብት ያገኘበት ቢሆንም የክልሉ ህዝብ በዚህ በኩል ካገኘው ጥቅም ይልቅ በሰብዓዊ መብት ጥሰት፣ በውሸት ፌዴራሊዝምና እና በሀብት ዘረፋ ከደረሰበት የከፋ በደል የተነሳ ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ያመዝናል ብለዋል፡፡

ጠ/ሚ አብይ አህመድ ግንቦት ሃያ የዘመናዊት ኢትዮጵያን ታሪክ ከቀየሩ ዕለታት መካከል አንዱ ነው ማለታቸው ይታወሳል፡፡

ግንቦት ሃያ የዘመናዊት ኢትዮጵያን ታሪክ ከቀየሩ ዕለታት መካከል አንዱ ነው ፤ ኢትዮጵያን ዴሞክራሲያዊ፣ፍትሐዊና ሰላማዊ ለማድረግ አያሌ ታጋዮች እጅግ ውድ የሆነውን የሰው ልጅ ነፍስ ሠውተዋልም ብለዋል ጠ/ሚ፡፡


ጠ/ሚ አብይ አህመድ አክለውም የግንቦት ሃያ ታጋዮች የነፍስ ዋጋ የከፈሉለት ዓላማ ግፍና ጭቆና፣አድሎና ወገንተኝነት ቆሞ፤ እኩልነት ፣ኅብረ ብሔራዊ አንድነት፣ ፍትሐዊ ተጠቃሚነትና የጋራ ብልጽግናን ለማረጋገጥ ነውም ብለዋል ፡፡

አውሎ ሚዲያ ግንቦት 20/2012 ዓ.ም

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ