ኢትዮጵያ ኮሮናቫይረስን ለመቋቋም የሩሲያ የሕክምና ዕርዳታን ትሻለች -በሩሲያ የኢትዮጵያ አምባሳደር አለማየሁ ተገኑ

0
197

ኢትዮጵያ ከኮቪድ-19 ጋር ያሉ በሽተኞች በቂ ምርመራና ሕክምና እንዲያገኙ ለማድረግና በመላ አገሪቱ ላቦራቶሪዎችን ለመክፈት ከሩሲያ ድጋፍ እንደምትፈልግ በሩሲያ የኢትዮጵያ አምባሳደር አለማየሁ ተገኑ ተናገሩ።

የሩሲያ መንግሥትና ሕዝብ ከኮቪድ-19 ጋር ለሚያደርጉት ትግል ከፍተኛ አድናቆት እንዳላቸውም አምባሳደሩለስፑትኒክ የዜና ምንጭ ተናግረዋል፡፡

ሩሲያም ወደ ብዙ የአፍሪካ አገራትና የተቀረው የዓለም ክፍል እየመጣች ነው ያሉት አምባሳደር ዓለማየሁ ኢትዮጵያ ከሩሲያ ፌዴሬሽን የምታገኘውን ድጋፍ ትጠብቃለች ብለዋል።

በሁለቱ አገራት መሪዎች መካከል በተደረገ ውይይት ተቀባይነት ማግኘቱንም አምባሳደሩ ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ ትንሽ አገር ሳትሆን የ110 ሚሊዮን ሕዝብ ያላት ትልቅ ሀገር ነች ያሉት አምባሳደሩ፤ “በተለያዩ ክልሎች ውስጥ በርካታ ላቦራቶሪዎችን ለመክፈት እንፈልጋለን ፡፡ ለእነዚህ የላቦራቶሪዎች መሣሪያዎች፣ የመመርመሪያ ቁሳቁሶችና አልባሳት ለሕክምና ባለሙያዎች በጣም አስፈላጊ ናቸው። እናም በዚህ ረገድ ዕርዳታ በጣም አስፈላጊ ነው።” ሲሉ አምባሳደር ዓለማየሁ ተናግረዋል።

አዉሎ ሚዲያ ግንቦት 20/2012 ዓ.ም

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ