ለግንቦት 20 የተከፈለው መስዋእትነት ግቡ ሳይመታ መክኗል አሉ ፕ/ር መረራ ጉዲና

0
134

 በአገሪቱ ባለፉት 27 ዓመታት በዕኩልነት ላይ የተመሰረተ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት መገንባት ባለመቻሉ ለግንቦት 20 ድል የተከፈለው መስዋትነት ባክንዋል አሉ ፕ/ር መረራ ጉዲና።

ከዘውዳዊው አገዛዝ ማብቂያ ማግስት ጀምሮ ባለፉት 50 ዓመታት የመጡ አገራዊ ለውጦች በዋናነት የከሸፉት በዕኩልነት ላይ የተመሰረተ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ባለመገንባቱ ነው ያሉት ፕ/ር መረራ ጉዲና አክለውም  በንጉሡ ዘመነ መንግሥት በዋናነት የወጣቱ ጥያቄ የዕኩልነትና መሬት ላራሹ የሚል የነበረ ቢሆንም የመጣውን ለውጥ ደርግ ነጥቆ የራሱን አብዮት ለ17 ዓመት አካሂዶበታል ብለዋል።

የፖለቲካ ሳይንስ ምህሩ ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና  ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፤ ወጣቶች ጫካ ገብተው መራራ ትግል በማድረግ የ17 ዓመቱን የጭቆና አገዛዝ ገርስሰው ቢጥሉም፤  ባለፉት 27 ዓመታት በዕኩልነት ላይ የተመሰረተ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ባለመገንባቱ ለግንቦት 20 ድል የተከፈለው መስዋትነት መክንዋል ብልዋል።

አዉሎ ሚዲያ ግንቦት 20/2012 ዓ.ም

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ