የገንዘብ ገደቡ መጣሉን ተከትሎ መደረግ ያለባቸው ጥንቃቄዎች ምንድን ናቸው?

0
103

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ግንቦት 11 ቀን 2012 ዓ.ም ይፋ ባደረገው መመሪያ ከባንኮች በሚወጣ ገንዘብ ላይ ገደብ ተጥሏል። በመመሪያው መሰረት አንድ ግለሰብ በቀን ሁለት መቶ ሺህ ብር እንዲሁም በወር አንድ ሚሊዮን ብር ማውጣት ይችላል።

ለኩባንያዎች ደግሞ በቀን ሶስት መቶ ሺህ ብርና በወር ሁለት ነጥብ አምስት ሚሊዮን ብር እንዲያወጡ ይፈቀድላቸዋል። ግለሰቦችም ሆኑ ኩባንያዎች ከተፈቀደው በላይ ገንዘብ ለማንቀሳቀስ ቼክ፣ ሲፒኦ እና ከአካውንት ወደ አካውንት ማስተላለፍን መጠቀም ይገባቸዋል።

ከዚህ በተጨማሪም በቀን ውስጥ ግለሰቦችም ሆኑ ኩባንያዎች ከተፈቀደው በላይ ገንዘብ እንዲያወጡ አስገዳጅ ነገር ከገጠማቸው በባንኮች ፕሬዚዳንት ውሳኔ መሰረት ሊስተናገዱ ይችላሉ። የገደቡ አስፈላጊነትም በአገሪቱ ከገንዘብ ጋር የተያያዙ ወንጀሎችን ለመከላከልና ሕገ ወጥ የገንዘብ ዝውውርን ለመቆጣጠር እንዲቻል መሆኑን ባንኩ አስታውቋል።

መመሪያው የታለመለትን ዓላማ ማሳካት እንዲችል አፈፃፀሙ ትኩረት እንደሚያስፈልገውና መሟላት የሚገባቸው ቅድመ ሁኔታዎች እንዳሉም የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች ያስረዳሉ።

በደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚክስ መምህር የሆኑት ዶክተር አረጋ ሹመቴ እንደሚሉት፤ መመሪያው ከባንክና ከገበያ ውጭ የሚዘዋወረውን የገንዘብ መጠን በማሳነስ ሕገ ወጥ የገንዘብ ዝውውርን ለመቀነስ ይረዳል።

ግለሰቦችና ድርጅቶች ወደ ሕጋዊ የግብይት ስርዓት እንዲገቡ በማድረግ ታክስ እንዳይደበቅ ያግዛል፤ የመንግሥትን ግብር የመሰብሰብ አቅም ያሳድጋል። መሰረተ ልማቱ የተሟላ ባይሆንም መመሪያው ወደ ኤሌክትሮኒክ የክፍያ ስርዓት ለመግባት ያስገድዳል።

አዉሎ ሚዲያ ግንቦት 19/2012 ዓ.ም

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ