‘የተፈጥሮ ሃብታችንን ፍትሃዊና ምክንያታዊ በሆነ መንገድ ለመጠቀም የማንንም ፍቃድ መጠየቅ አያስፈልገንም’-የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገዱ አንዳርጋቸው

0
68

የሕዳሴው ግድብ የሁሉም ኢትዮጵያዊያን አጀንዳ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገዱ አንዳርጋቸው ገለፁ።

ሚኒስትሩ ይህን የገለጹት ለተፎካካሪ የፖለቲካ ፖርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አባላት ግድቡን አስመልክቶ እየተከናወኑ ስለሚገኙ የዲፕሎማሲ ስራዎች ባደረጉት ገለፃ ነው።

ኢትዮጵያ የግድቡን ግንባታ ከመጀመሯ በፊት የዲፕሎማሲ ስራዋን መጀመሯን አስታውሰው አሁንም ይኸው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።

‘የተፈጥሮ ሃብታችንን ፍትሃዊና ምክንያታዊ በሆነ መንገድ ለመጠቀም የማንንም ፍቃድ መጠየቅ አያስፈልገንም’ ያሉት ሚኒስትሩ ‘የግድቡ ግንባታ ሌሎችን የመጉዳት ዓላማ እንደሌለው ለዓለምአቀፋ ማኅበረሰብ እያሳወቅን ነው’ ብለዋል።

የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለም የግድቡን የቴክኒክ ደረጃ አስረድተዋል።

የጋራ ምክር ቤቱ ሰብሳቢ ሙሳ አደም በበኩላቸው ‘የፖለቲካ ፖርቲዎች በግድቡ ላይ ያለንን አንድነት በተግባር የምናሳይበት ጊዜ ነው’ ብለዋል።

በዚህ ወቅት ከአገር ሉዓላዊነት በላይ ቅድሚያ የሚሰጠው አጀንዳ ባለመኖሩ ሁሉም ዜጋ ከውጭ የሚመጣውን ተጽዕኖ በጋራ መመከት አለበት ሲሉም ተናግረዋል።

እየተካሄደ ያለው ውይይት በተፎካካሪ ፖለቲካ ፖርቲዎች የጋራ ምክር ቤትና በግድቡ ሕዝባዊ ተሳትፎ ብሔራዊ ምክር ቤት ትብብር የተዘጋጀ ነው።

አዉሎ ሚዲያ ግንቦት 19/2012 ዓ.ም

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ