በኦሮሚያ ክልል በመንግስት የፀጥታ ሀይል የሚፈፀም ግድያ እና አፈና እየበዛ ነው ተባለ

0
96

በኦሮሚያ ክልል በኦሮሚያ ልዩ ሀይልና በመከላከያ ሰራዊት አማካኝነት ግድያና አፈና እየተፈፀመ ነው እንደሆነ የኦነግ የፖለቲካ ኦፊሰር ለአዉሎሚዲያ ተናግረዋል።

የኦነግ የፖለቲካ ኦፊሰር የሆኑት አቶ ዳዊት አብደታ ከአዉሎ ሚዲያ ገር በነበራቸው ቆይታ በአዲስ አበባ ብቻ የኦነግ አባላትና ደጋፊ የሆኑ 169 ሰዎች ታስረዋል ብለዋል።

በኦሮሚያ አንፊሎ/ ገሌ አካባቢ ሶስት ወጣቶች እጃቸውን የፍጥኝ ታሰረው ከተወሰዱ በኋላ ጠዋት ላይ ተገድለው ተጥለዋል ነው ያሉት።

ላሎ በሚባለው አካባቢ የብርብ ቀበሌ ኗሪ የሆኑት ወይዘሮ አምሳለ ጉደታም በመንግስት የፀጥታ ሀይል ታፍነው ከተወሰዱ በሗላ ጠዋት ላይ ተገድለው ተገኝተዋል ሲሉ ነው የነገሩን።

በሌላ በኩል በበምስራቅ ሀረርጌ ባብሌ መሐመድ አሚን የተባለ የመንግስት ሰራተኛም ተገድሎ ተጥሎ ተገኝተዋል በማለት የተናገሩት አቶ ዳዊት አብደታ በምዕራብ ወለጋ ዋንጆ ጃርሶ አካባቢም አራት መኖሪያ ቤቶችና የንግድ ቤቶች በመንግስት የፀጥታ አካላት ተቃጥለዋል ነው ያሉት።

አቶ ዳዊት ከአውሎ ሚዲያ “ስለ ሀገር” በተሰኘው ፕሮግራም ላይ ቆይታ ያደረጉ ሲሆን በክልሉ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በመጠቀም መንግስት ተገቢ ያልሆነ ስራ እየሰራ ነው አፈና እና ግድያ እየፈፀመ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

አዉሎ ሚዲያ ግንቦት 18/2012 ዓ.ም

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ