የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ናታንያሁ ለመጀመሪያ ግዜ ችሎት ቀረቡ

0
190

የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ናታንያሁ በሙስና ወንጀል ችሎት ለመጀመሪያ ጊዜ በኢየሩሳሌም ፍርድ ቤት መቅረባቸው አንዳሎ ኤጀንሲ ዘግቧል ፡፡

የእስራኤሉ ደይሊ ሀርቴዝ እንዳለው “በሀገሪቱ ታሪክ ውስጥ ለመጀመፘ ግዜ አንድ ጠቅላይ ሚኒስትር በወንጀል ተጠርጥሮ ችሎት ፊት ቀርቧል ” ብልዋል ፡፡
ነታንያሁ እና ጠበቆቹ በችሎቱ ላይ ተገኝተው የነበረ ሲሆን የእስራኤል እና የዓለም አቀፉ ሚዲያዎችም ሽፋን ለመስጠት በቦታው ትግውኝተዋል ነው የተባለው ፡፡ ለኒታንያሁ ድጋፍ ለመስጠትም በርካታ የመንግስት ሚኒስትሮች እና የህግ ባለሙያዎች ተገኝተዋል ፡፡

በችሎቱ ፊት የቆሙት ናታንያሁ ለፖሊስ እና ለዐቃብያነ ሕግ በእኔ ላይ በማሴር ክስ መመስረታቸው ልክ አይደለም ሲሉ በቀጥታ ስርጭት ጠይቋል ፡፡

የናታንያሁ የፍርድ ሂደት መጋቢት 17 ቀን መጀመር የነበረበት ሲሆነ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ግን እስካሁን ተራዝሞ ቆይቷል ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ናታንያሁ ጉቦን ፣ የእምነትጥሰት እና ማጭበርበርን በሚያካትቱ በሶስት ጉዳዮች የተከሰሱ ሲሆን እሳቸው ግን በጠበቃቸው በኩል ድርጊቱን አለመፈፀማችወ እየተናገሩ ይገኛሉ፡፡

በሚያዝያ ወር ውስጥ ናታንያሁ እና የተቃዋሚ መሪው ቤኒ ጋንትዝ የብሔራዊ አንድነት መንግሥት ለመመስረት ተስማሙ ፡፡

የገዥው ፓርቲ ፓርቲ ሊኲድ(Likud )ፓርቲ ሊቀመንበር የሆኑት ናትናንያ እና የሰማያዊ እና የነጭ ፓርቲ ሃላፊ የሆኑት ጋንትዝ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ሶስት የቅድመ ምርጫ ምርጫዎችን ካካሄዱ በኋላ መንግስት ለመመስረት መስማማታቸው የታወሳል ፡፡ ዜናው አንዳሎ ኤጀንሲ ዋቢ አድርጎ ሚድል ኢስት ሞኒተር ዘግቦታል።

አዉሎ ሚዲያ ግንቦት 17/2012 ዓ.ም

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ