የትግራይ ክልል በመንግስት ሚዲያዎች የትግራይን ህዝብ በተመለከተ ሀሰተኛ መረጃ እየተሰራጨ ነው አለ

0
111

የክልሉ መንግስት ዛሬ ባወጣም መግለጫ ከመጋረጃ በስተጀርባ በተፈበረከ ሐሰተኛ፣ የበሬ ወለደ ወሬ የሚደናገር ህዝብ ፈፅሞ አይኖርም ያለ ሲሆን ባለፉት ሁለት ዓመታት፣ የተቀነባበረ፣ ሓሰተኛ ዴክሜንታሪ ፊልም ሰርቶ በማሰራጨት፣ በትግራይ ህዝብና መንግስት ላይ ሲሰነዘር የነበረው ብሄር ተኮር ጥቃት፣ አሁንም ዳግሞ እየተፈፀመ ነው በሏል።

ትላንት ግንቦት 16/2012 ዓ/ም፣ በተመሳሳይ ቀንና ሰዓት፣ በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን፣ በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት፣ በፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን፣ በዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል፣ በብልፅግና ፓርቲ ፌስቡክ ፔጅ፣ በኣዲስ ኣበባ ብልፅግና ፓርቲ ፌስቡክ ፔጅ፣ በአማራ መገናኛ ብዙሃን እንዲሁም ከግል ሚዲያዎች፣ ማለትም በኢሳት፣ በአባይ ሚዲያ፣ በዘሀበሻ ወዘተ የሚባሉ እንዲሁም መረጃ ዶት ኮም እና አዲስ ፋክት በተባሉ ማህበራዊ ሚዲያ ትግራይ ላይ ህዝባዊ አመፅ አየተካሔደ ነው በሚል ሀሰተኛ መረጃ ተሰራጭቷል ነው ያለው ።

ይህንን ያሰራጩት በአንድ ሳምባ የሚተነፍሱ ሚዲያዎች ናቸው ያለው ህወሓት በትግራይ ክልል የተለያዩ አከባቢዎች የፀጥታ መደፍረስ መፈጠሩ ተገለፀ፣ በተለያዩ አከባቢዎች ማለትም በሽረ እንዳስላሰ እና አከባቢዎች፣ እንዲሁም በዋጅራትና አከባቢው ሰለማዊ ሰልፎች ተካሄዱ፣ ፍትህ መጓደል አለ ወዘተ፣ ስለዚህ ይህ ችግር ወደ ከፋ ደረጀ ከመሸጋገሩ በፊት የፌደራል መንግስት ጣልቃ እንዲገባ ጠየቁ በማለት፣ እንዲሆንላቸው የሚመኙትን ቅዠት፣ ራሳቸው ፈብርከው ሐሰተኛ መረጃ ተሰራጭቷል በማለት የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ገልጿል።

በኢትዮጵያ ህዝብ ሀብት የሚተዳደሩት እነዚህ የሚበዙት ሚዲያዎች ትላንት ያሰራጩት ሐሰተኛ ወሬ ባለፉት ሁለት ዓመታት የፌዴራል መንግስት እያሰተዳደረ ላለው አካል እና ለእነዚህ የሚዲያ ኣውታሮች፣ ትልቅ ራስ ምታት የሆነባቸውን በትግራይ ህዝብና መንግስት ያለው እንደ ብረት የጠነከረ ግንኙነት፣ ክፍተት ይፈጥርልናል ብለው፣ ትላንት ሐሰተኛ ወሬ ማሰራጨታቸው ከንቱ ልፋት ነው በማለትም በመግለጫው ተጠቅሷል።


አዉሎ ሚዲያ ግንቦት 17/2012 ዓ.ም

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ