በትግራይ ክልል እየተካሄደ ያለው ሕዝባዊ እንቅስቃሴ የነጻነትና የሥርዓት ለውጥ ፍላጎት ነው– አቶ ነብዩ ስሑል አንዳንድ ሚዲያዎች ትግራይ ክልልን አስመልክተው እያወጡት ያለው መረጃ የበሬ ወለድ ወሬ ነው—-ወ/ሮ ሊያ ካሳ

0
84

በትግራይ ክልል የብልፅና ፓርቲ ሀላፊ የሆኑት አቶ ነብዩ ስሑል ለአዲስ ዘመን እንደተናገሩት ፤ ብልጽግና የህዝቡ ድምጽ እንዲሰማ ጥያቄውንም ባግባቡ እንዲያቀርብ የማበረታታት፤ ክልሉን የሚያስተዳድረው መንግሥት ኃላፊነቱን እንዲወጣ የመወትወትና የማሳሰብ ሥራ እየሰራ ነው ብለዋል።ሀላፊው አክለውም ‹‹ከእዚህ በላይ መሄድ የሚቻልበት ዕድል ሊኖር ይችላል የሕዝብ ችግር በጊዜው መፈታት አለበት›› ሲሉም አሳስበዋል። ችግሩ የማይፈታ ከሆነ እንደብልጽግና የሕዝቡን ችግር የመፍታት ኃላፊነት ስላለብን ህጋዊ እንቅስቃሴ ወደማድረግ እንሸጋገራለን ብለዋል።

የትግራይ ኮሚኒኬሽን ቢሮ ሃላፊዋ ው/ሮ ሊያ ካሳ በፌስ ቡክ ገፃቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ “የዚች አገር ሚድያዎች በበሬ ወለደ የትግራይ ህዝብና መንግስት ለማንበርከክም ሆነ በትግራይ ተወላጅ ሌላዉ እንዲዘመት የክተት አዋጅ እያወጁ ቆይተዋል ይህ የሳምንቱ ዘመቻም አንዱ አካል ነው ” በለዋል።

ሀላፊዋ ጨምረው ልብ ሊባል የሚገባዉ ጉዳይ ቢኖር የትግራይ ህዝብና መንግስት የክልሉን ሰላም ለማደፍረስ ከዉስጥም ከዉጭም ለሚንቀሳቀስ ሃይሎች ከቶም አንፈቅድም ብቻም ሳይሆን በዚህ ሁለት አመት ዉስጥም ትግራይ የግጭትና ብጥብጥ መናሃርያ እንድትሆን ሌት ተቀን ሴራ ሲሽርቡ ነብር፤ ትግራይ የሰላም ተምሳሌት የመሆንዋ ሚስጥር የትግራይ ህዝብ ለሰላም የከፈለዉ ዋጋ ጠንቅቆ ሰለሚያዉቅ ፣ አንድነቱ በማጠናከር ከመንግስቱና መሪ ድርጅቱ ጎን በመሆን ለሰላሙና ድህንነቱ ዘብ የቆመ ጀግና ህዝብ መሆኑ አትዘነጉቱም እና ከንቱ ልፍት ነዉም ብለዋል።

አቶ ንብዩ ስሑል በበኩላችው ሕዝቡ በችግሩ ውስጥ ተዘፍቆ መቆየት የለበትም የሚል ጽኑ ዕምነት ስላለ የክልሉ መንግሥት የሚያስተዳድረውን ሕዝብ ጥያቄ መመለስና ሕዝቡም መፍትሄ ማግኘት አለበት ፤ የክልሉ መንግሥት የሚያስተዳድረውን ሕዝብ ጥያቄ መመለስ የሚያቅተው ከሆነ ሕዝቡ መፍትሄ ማግኘት ስላለበት ብልጽግና እንደመንግሥት ሕጋዊ መንገድን በመከተል የሚቻለውን ለማድረግ እየተዘጋጀ መሆኑን ጠቁመዋል።

ከተጀመረ ወራት ስላስቆጠረው የትግራይ የወረዳ አደረጃጀት የመለውጥ ስራ የክልሉ ምክትል ር እሰ መተዳድር ዶ/ር ደብረፂዮን እየተሰራ ይገኛል ማለታቸው ይታወሳል። በዚህም የወረዳ ማዕከላት ከተመረጡ በኋላ እነዚህን ተከትሎ ወረዳዎች እንዳዲስ እንዲደራጁ ሆኗል። በዚህ ሂደት መነሻ ጥናቶች ቢኖሩም የመጨረሻ ውሳኔው የህዝቡ ነው ተብሎ፤ ቀበሌዎች ወደ መረጡት ወረዳ እንዲካለሉ እየተደረገም ነው ማለታችው ይታወሳል ።

ባለፉት ሶስት ቀናት በትግራይ ክልል ህዝባዊ አመፅ አለ ተብሎ በፌዴራል መንግስት ሚዲያዎችና አክቲቪስቶች እየተወራ ቢሆንም የትግራይ ክልል መንግስት ባለስልጣናቱ ግን ሀሰት ነው እያሉ ነው።

የአረና ፓርቲና የብልፅግና ፓርቲ ሀላፊዎች “አመፅ አለ ፤ አመፁ እየተመራ ያለው ፈንቅል በተባለ የተደራጀ ቡድን ነው ቢሉም አዉሎ ሚዲያ ለሚበመለው ነገር ግን ትክክለኛ መረጃ አላገኘም።

አዉሎ ሚዲያ ግንቦት 17/2012 ዓ.ም

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ