በስፔን በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ቤት መቀመጥን በመቃወም ሰልፍ አካሄዱ

0
195

ስፔን በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የአገሪቷ መንግሥት የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመቆጣጠር እየሰራ ያለውን ተግባር በመቃወም የተቃውሞ ሰልፍ አካሂደዋል፡፡

የተቃውሞ ሰልፈኞቹ አካላዊ ርቀታቸውን እንዲጠብቁ ከመኪናቸው ሳይወርዱ በተለያዩ ከተሞች እንዲያሽከረክሩ ‘ፋር ራይት ቮክስ’ ፓርቲ ደጋፊዎቹን አሳስቧል፡፡

በመሆኑም በዋና ከተማዋ ማድሪድ ተቃዋሚዎች የስፔንን ሰንደቅ አላማ በመያዝ መኪና እያሽከረከሩ የታዩ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስተር ፔድሮ ሳንቼዝ ሥልጣናቸውን እንዲለቁ ጠይቀዋል፡፡

ስፔን በጎርጎሳውያኑ መጋቢት 14 ወረርሽኙን ለመቆጣጠር ከሌሎች አውሮፓ አገራት ጥብቅ የሆኑ ውሳኔዎችን አስተላልፋለች፡፡

ይሁን እንጅ ባለፉት ሳምንታት የጣለቻቸውን ገደቦች አላልታለች፡፡ ሆኖም ማድሪድና ባርሴሎና ግን በወረርሽኙ ክፉኛ በመጠቃታቸው አሁንም ጥብቅ በሆነ የእንቅስቃሴ ገደብ ውስጥ ይገኛሉ፡፡

ነገር ግን ሁለቱ ከተሞች ከሰኞ ዕለት ጀምሮ ከቤት ውጭ መመገብንና እስከ አስር የሚደርሱ ሰዎች መሰባሰብን በመፍቀድ የጣሉትን ገደብ ማላላት ይጀምራሉ ተብሏል፡፡

አገሪቷ በጣለችው የሁለት ወራት በቤት ውስጥ የመቀመጥ ገደብ፤ ሆቴሎች፣ መጠጥ ቤቶች፣ ምግብ ቤቶች እንዲሁም የባህር ዳርቻዎችና ሌሎች የመዝናኛ ሥፍራዎች ተዘግተዋል፡፡

መንግሥት ይህን ያደረገው ወረርሽኙን ለመቆጣጠር እንደሆነ በመግለጽ በአንድ ቀን የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር እየቀነሰ መሆኑን አስታውቋል፡፡

የፓርቲው መሪ ሳንቲያጎ አባስካል በማድሪድ ክፍት በሆነ አውቶብስ ተቃዋሚዎቹን ሲመሩ ታይተዋል፡፡ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ (ማስክ) አድርገው የታዩት መሪው፤ “መንግሥት ወረርሽኙን ለመቆጣጠር ባከናወነው ደካማ ተግባር በቀጥታ ተጠያቂ ነው” ሲሉ ከሰዋል፡፡

በተመሳሳይ በስቪሌ፣ ባርሴሎና እና ሌሎች ከተሞችም ተቃውሞዎች ተካሂደዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስተር ሳንቼዝ ተቃውሞውን ተከትሎ ሁለት ዋና ዋና ገደቦችን እንደሚያላሉ አስታውቀዋል፡፡

አዉሎ ሚዲያ ግንቦት 17/2012 ዓ.ም

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ