የኢራኑ ሹራ ካውንስል ፀረ እስራኤል ህግ እንደሚደግፍ አስታወቀ

0
140

ምክር ቤቱ ትላንት ባደረገው ስብሰባ እስራኤል በአከባቢው እና በአለማቀፍ ደረጃ በደህንነት ዙረያ ለምትሰራቸው ተቃራኒ ድርጊቶች የሚቃወም ረቂቅ ህግ ማፅደቁ ተነግረዋል፡፡

የኢራኑ ሹራ ምክርቤት ባወጣው ረቂቅ አዋጅ አንቀፅ አንድ እንዲህ ይላል *እስራኤል በተጎሳቆሉ አካላት ፣ በኢስላማዊ ሀገራት እንዲሁም በኢራን ኢስላማዊ ሪፓብሊክ ላይ የምታራምዳቸውን አጥፊ ተግባራት ለመቋቋም ፅዮናዊ አካል የሚባል የትኛውም እንቅስቃሴ ለሚቃወም ድጋፍ ይደረግለታል *ይላል፡፡

አንቀፁ በተጨማሪም በእስራኤል የተያዙት የፍልስጤም ግዛቶች ፣ በሶርያና በሊባኖን ግዛትዋ ለማስፋፋት የሞከረችው ሙከራም አጥብቆ እንደሚቃወም ይገልፃል፡፡

በህጉ አንቀፅ ሁለት የኢራኑ ሹራን ካውንስል  የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር በ6 ወር ውስጥ ዝግጅት አድርጎ የፍልሰጤማዊያን በሆነው አየሩሳሌም ከተማ ኤምባሲ እንዲከፍት ሲልም  ወስንዋል፡፡ ዘገባው የሚድል ኢስት ሞኒተር ነው

አዉሎ ሚዲያ ግንቦት 11/2012 ዓ.ም

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ