በቺሊ የሳንድያጎ ነዋሪዎች የከቤት እንዳትወጡ የሚለውን ትእዛዝ ጥሰው ጎዳና ላይ ለአመፅ ወጡ

0
182

በቺሊ ዋና ከተማ በብዛት በኢኮኖሚ ዝቅተኛ የሆኑ ማህበረሰብ የሚኖርበት ሰፈር የምግብ እና የመድሃኒት አቅርቦት እንሻለን በሚሉ ነዋሪዎች ዛሬ ከፍተኛ ተቃውሞ እንደተነሳ አልጀዚራ ዘግቧል፡፡

የችሊ መንግስት የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ለመግታት ሲባል ህዝቡ ከቤት እንዳይወጣ ማለቱ ተከትሎ የሚበላ አጥተናል ክፉኛም ተርበናል በሚሉ ሰዎች ስላማዊ ሰልፉ የተነሳ ሲሆን፣ ፖሊስ ሰልፈኞቹ ለመበተን በሞከረበት ሰዓት ፖሊስ ከሰልፈኞቹ ጋር ግጭት ውስጥ መግባቱ ተሰምቷል፡፡

የቺሊ ፕሬዚደንት ሴባስትያን ፒናራ ቀድሞውኑ እርዳታ እንደሚያደርጉላቸው ቃል የገቡ ቢሆኑም ፤ የገቡትን ቃል ባለመፈፀማቸው ህዝቡ ለአመፅ እንደ ተነሳ የሃገሪትዋ ፖለቲከኞች ተናግረዋል፡፡

ቺሊ እስካሁን ማለትም ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ስአት 46 059 ዜጎቿበኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሲሆን 478 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ምክንያት ሂዎታቸው አልፏል፡፡

አዉሎ ሚዲያ ግንቦት 11/2012 ዓ.ም

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ