በምስራቅ አፍሪካ ኮሮና ቫይረስ በፍጥነት እየተስፋፋ ነው

0
174

ኮሮና ቫይረስ በዓለማቀፍ ደረጃ ለሰውልጅ አደጋ ከደቀኑ ወረርሽኞች ቀዳሚ ስለመሆኑ የህክምና ጠበብቶች የሚስማሙበት ሀቅ ነው፡፡ ታድያ ይህ ወረርሽኝ ከቻይናዋ ዉሀን ግዛት ከተቀሰቀሰበት ግዜ ጀምሮ እስካሁን ዓለም ከ4 ሚሊዮን 910 ሺ  በላይ ዜጎቼ በኮሮና ቫይረስ ተይዞብኛል ስትል በዓለምጤና ድርጅት በኩል በየቀኑ ሪፖርት ማድረግ ከጀመረች ውራቶች ነጉዷል፡፡

ከ320 ሺ በላይ ደግሞ በዚህ አስከፊ በሽታ ኮሮና ቫይረስ ምክንያት ሕይወታቸው አልፏል፤ ወደ 2 ሚሊዮን የሚጠጉት ደግሞ እድል ቀንታቸው ከበሽታው ለማገገም ችለዋል፡፡

ይህ ቫይረስ 213 የዓለም ሀገራት አካሏል ፡፡አፍሪካም በእንቅርት ላይ ጆሮደገፍ ይሉት የዚህ ገፈት ቀማሽ ሁና ከ86 ሺ በላይ ህዝባዋ ለኮሮና ቫይረስ ገብራለች ፡፡

የዓለም ጤና ድርጅት እና የምስራቅ አፍሪካ በይነ መንግስታት (ኢጋድ) ባሳላፍነው ወር የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በምስራቅ አፍሪካ የመስፋፋቱ አዝማሚያ አደገኛ ማለቱ ይታወሳል፡፡

በዚሁ ቀጠና ማለትም በምስራቅ አፍሪካ በኮሮና ቫይረስ በብዛት ዜጎቿ የተያዙባት ሀገር ሱዳን ስትሆን ከ 2500 ሰዎች በላይ መያዛቸው ሪፖርት አድርጋለች፡፡ ጅቡቲ  ከ1500 በላይ ሰዎች የተያዙባት ሁለተኛ ሀገርናት፡፡ በሶስተኝነት የምትክተለው ሶማልያ ከ 1400 በላይ ሰዎች ተይዞብኛል ስትል ሪፖርት አድርጋለች፡፡ኬንያ ከ900 በላይ ሰዎች በኮሮ ተይዞብኛል ያለች አራተኛ ሀገር ናት፡፡

በእድሜ ትንሽዋ ምስራቅ አፍሪካዊትዋ ሀገር ደቡበ ሱዳን ከፍተኛ ባለስልጣን ፣ መሪዎችዋ ሳይቀሩ በኮሮ ቫይረስ መያዛቸው ሪፖርት ማድረግዋ የታወሳል፡፡ ኤርትራ 39 በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ነበሩ አሁን ግን ሁሉንም አገግመው በግዛቴ ውስጥ አንድም በኮሮና ቫይረስ የተያዘ ሰው የለም ስትል ባሳለፍነው ሳምንት ሪፖርት አድርጋለች፡፡

 ሀገራችን ኢትዮጵያ ከሌሎች አንፃር ደህና የሚባል በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቢኖረዋትም የጎረቤት ሀገራት የቫይረሱ በፍጥነት መስፋፋት እና የህዝቡ ቸልተኝነት ተደማምሮ ግን በሀገራችን የቫይረሱ የመስፋፋት እድሉ አስፈሪ ያደርገዋል ፡፡ይህ ዜና በሚጠናቀርበት ሰአት በሀገራችን ኢትዮጵያ 365 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተይዞብኛል ስትል ሪፖርት አድርጋለች፡፡ለዜናው ጥንቅር east Africa corona vairus riport ተጠቀምን፡፡

አውሎ ሚዲያ ግንቦት 11/2012 ዓ.ም

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ