ኮሮና በሴቶች ላይ ይፈጸም የነበረን ጥቃት አባብሶታል ተባለ

0
164

በሶስት ወራት ውስጥ ብቻ 15 ሚሊዮን የቤት ውስጥ ጥቃቶች ተፈጽመዋል
በዘመነ ኮሮና በሴቶች ላይ ይፈጸሙ የነበሩ የቤት ውስጥ ጥቃቶችን ተባብሰዋል። ባለፉት ሶስት ወራት 15 ሚሊዮን የቤት ውስጥ ጥቃቶች ተመዝግበዋል ።

ይህ የሆነው ደግሞ ከቫይረሱ ስርጭት ጋር ተያይዞ ወረርሽኙን ለመከላከል በተጣሉት ገደቦች ምክንያት ነው። በዚህም ባለፉት ሶስት ወራት ውስጥ 15 ሚሊዮን የቤት ውስጥ ጥቃቶች ተመዝግበዋል። በሴቶች ላይ የሚፈጸመው ጥቃት ለአለም የማህበረሰብ ጤና ትልቅ እንቅፋት እየሆነም ነው።

ወረርሽኙ በሴቶች ላይ አሰቃቂ ተፅእኖ ይኖረዋል ሲል የዓለም ጤና ድርጅት አስጠንቅቋል። በዚህም የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት ሰዎች በቤታቸው እንዲቀመጡ ሲደረግ በተለይም ሴቶች በቤት ውስጥ እንዲቀመጡ በመደረጋቸው ብቻ 20 በመቶዎቹ ለቤቱ ውስጥ ጥቃት ተጋልጠዋል።

የአለም አቀፉ ማህበረሰብ በሴቶች ላይ እየደረሰ ያለውን ጥቃት ለመከላከል ትኩረት ሰጥተው መስራት እንደሚያስፈልግ የዘርፉ ባለሙያዎች እየተናገሩ ነው። የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች እንደሚሉት፣ በወረርሽኙ ምክንያት በሴቶች ላይ እየደረሰ ያለው ጫና በከፍተኛ ሁኔታም እየተባባሰ ነው።

ከኮሮና ቫይረስ ቀውስ ለማገገም የሥርዓተ- ጾታ ስርዓትን ማሻሻልና ማጎልበት እንደሚያስፈልግ ብዙዎች ይስማማሉ።እንደዚህ ዓይነት ማህበራዊ ከስተቶችን ስንመለከት በመጀመሪያ የችግሩ ተጎጂዎች ሴቶች በመሆናቸው ትኩረት አድርጎ መስራት ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ይጠበቃል።

በተለይም ከድህነት፣ ከዘር ወይም ከአካል ጉዳተኝነት ጋር በተዛመዱ ለበርካታ መድልዎ ዓይነቶች የተጋለጡ ሰዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመር ሲሆን በሴቶች ላይ የሚፈጸሙት ጥቃቶች ከፍተኛውን ቁጥር ይወስዳሉ። የቅርብ ጊዜያት መረጃዎች እንደሚያሳዩት 30 በመቶ የሚሆኑት በሆነ ወቅት ላይ ከአጋሮቻቸው አካላዊና ወይም ወሲባዊ ጥቃት ደርሶባቸዋል። በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ግን ከዚህ የተለየ ነው።

 በዚህ ልዩ ባህርይ አሁን ያለው የጤና ቀውስና ተጓዳኝ እርምጃዎች በተለይም ሴቶች በዓለም ዙሪያ በሚኖሩበት አኗኗር ላይ ምን ያህል ተጽዕኖ እንዳሳደሩ መገንዘብ አዳጋች አይሆንም።

ቀድሞውኑ በቤት ውስጥ ጥቃት ብዙ ሴቶች ችግር እየደረሰባቸው ቢሆንም ቫይረሱን ለመከላከል በቤታቸው እንዲቆዩ መደረጋቸው ለችግሩ ይበልጥ ተጋላጭ አድርጓቸዋል።

 በዚህ ዘመን እራሳቸውን ችለው በሚኖሩ ቤተሰቦች ውስጥ የሚኖሩ ሁሉ የጥቃት ተጋላጭነታቸው ከፍተኛ ነው። በዓለም ዙሪያ ለሚከሰቱ የቤተሰብ ጥቃቶች በከፍተኛ ሁኔታ የመጨመር እድሉ ከፍተኛ ሆኗል።

አዉሎ ሚዲያ ግንቦት 10/2012 ዓ.ም

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ