የኢትዮጵያ መንግዶች ባለስልጣን በ11 ነጥብ 6 ቢለየን ብር ወጪ የ7 መንገዶች ግንባታ ስምምነት ተፈራረመ

0
368

በዛሬው እለት የውል ስምምነት የተፈረመላቸው መንገዶቹ የሚገነቡት በአስፋልት ደረጃ ሲሆን፥ በአጠቃላይ 509 ነጥብ 11 ኪሎ ሜትር ርዝማኔ አላቸው።

ለግንባታቸው የሚውለው ገንዘብ ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያ መንግሥት የሚሸፈን መሆኑም በስምምነቱ ወቅት ተገልጿል።

 የውል ስምምነት የተፈረመላቸው መንገዶቹም፦

1. ደብረ ብርሃን- ደነባ- ለሚ መገንጠያ እና ጅሁር- ደነባ

2. ፊቅ- ሰገግ- ገርቦ ደነን (ሎት 3. ዮአሌ – ደነን)

 3. ሁምቦ- ጠበላ- አባያ-

4. ዳዬ- ግርጃ- ክብረ መንግስት (መልካ ደስታ) እና መለያ- መጆ መገንጠያ

5. ጅግጅጋ- ገለለሽ- ደገሃምቦ- ፈገግ (ኮንትራ 2)

 6. ሀወላቱላ- ወተራራሳ- ያዩ- ውራቼ 7. ዛላምበሳ- አሊቴና- መረዋ- እዳጋሃሙር (ሎት 1. ዛላምበሳ- አሊቴና መገንጠያ) ናቸው። የመንገዶቹ ግንባታ ለማጠናቀቀም ከሦስት እስከ አራት ዓመታት እንደሚወስድ ተጠቅሷል።

አዉሎ ሚዲያ ሚያዚያ 20/2012 ዓ.ም

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ