ዶ/ር አረጋ ይርዳው ከሜድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ከዋና ስራ አስፈፃሚነታቸው ተነሱ

0
110

ሼህ አልአሙዲ ጌታቸው ሐጎስን ሾመዋል አቶ ጌታቸው ሐጎስ የሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ጊዜያዊ ሲኢኦ አድርገው መሾማቸውን ሼህ ሙሐመድ ሁሴን አሊ አልአሙዲ አስታወቀዋል።

ሼህ ሙሐመድ ከ20 ዓመታት በላይ ቴክኖሎጂ ግሩፑን የመሩትን የዶ/ር አረጋን መልቀቂያ መቀበላቸውን ባሳወቁበት ደብዳቤ እንደገለፁት ዶ/ር አረጋ ይርዳው የዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ ኘረዝደንት ሆነው እንደሚቀጥሉ ተስማምተዋል።

ዶ/ር አረጋ እየደረሰብኝ ባለው ጫና ምክንያት ስራዬን በትክክል መስራት አልቻልኩም ብለው መልቀቂያ ያስገቡ ሲሆን በዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ ኃላፊነታቸው ለመቀጠል ያላቸውን ፍላጎት ገልፀው ነበር።

አዉሎ ሚዲያ ሚያዚያ 19/2012 ዓ.ም

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ