በኢትዮጵያ በቢጫ ወባ በሽታ 86 ሰዎች ተይዘዋል-የጤና ሚኒስቴር

0
137

በኢትዮጵያ በቢጫ ወባ በሽታ 86 ሰዎች መያዛቸውን  የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ።

ዶክተር ሊያ በደቡብ ክልል ጉራጌ ዞን አነሞር እና ኢነር ወረዳ ከየካቲት ወር መጨረሻ ጀምሮ የበሽታው ምልክት መታየቱን ሪፓርት መደረጉን ገልፀዋል። በዚህም የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዪት ከክልሉ ጤና ቢሮ እና ከዞኑ ጤና መምሪ ጋር በመሆን የምላሽ አሰጣጡን ሲደግፍ እንደነበረም ተናግረዋል።

በመሆኑም የካታት 24  እንደጀመረ ያስታወቁ ሲሆን ለመጨረሻ ጊዜ በበሽታው የተያዘ ሰው ሪፓርት የተደረገው መጋቢት 20  እንደሆነ አስታውቀዋል። በዚህም እስከአሁን 86 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው እና አራት ሰዎችም ህይወታቸው ማለፉን ሚኒስትሯ በፌስቡክ ገፃቸው ላይ አስፍረዋል።

የአለም ጤና ድርጅት የሳምንቱ ሪፖርት እንድሚያሳየው በአለም ደረጃ የወባ አስጊነት ከፍ ብልዋል ሀገራት ለወባም ትኩረት እንዲሰጡ ማሳሰብያ ጭምር መስጠቱ ይታወሳል ሲል fbc አስነብቧል።

አዉሎ ሚዲያ ሚያዚያ 19/2012 ዓ.ም

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ