ሚሊዮኖች ቫይረስ የሚከታተለውን መተግበሪያ ስልካቸው ላይ እየጫኑ ነው

0
86

አውስትራሊያ ውስጥ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ሰዎች የኮሮናቫይረስ ንክኪ የሚቆጣጠረውን መተግበሪያ ስልካቸው ላይ እየጫኑ ነው።

ኮቪድሴፍ የተሰኘው መተግበሪያ ሁለት ሰዎች ሲገናኝ ብሉቱዝ የተሰኘውን ቴክኖሎጂ ተጠቅሞ በስልኮቻቸው ‘እንዲጨባበጡ’ ያስችላቸዋል። አልፎም የሰዎችን መረጃ በመበርበር ለባለቤቱ ያሳውቃል።

ይህም ማለት ተጠቃሚዎች በሄዱበት ሁሉ ማን ኮሮናቫይረስ እንዳለበትና እንደሌለበት፣ ማን እንዳገገመ ማወቅ ይችላሉ።

አውስትራሊያ እስካሁን ድረስ 6694 ሰዎች በኮሮናቫይረስ መያዛቸውን ይፋ አድርጋለች። 80 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ምክንያት ሕይወታቸው አልፏል።

መንግሥት የሰዎችን መረጃ የምፈልገው ቫይረሱን ለመቀነስ፤ ከዚያ በኋላ አጠፋዋለሁ እያለ ነው። ተቺዎች ግን የግለሰቦች መረጃ እየተጠበቀ አይደለም፤ ሕጉም ፓርላማው እየሠራ ባለመሆኑ አልፀደቀም ሲሉ ይከራከራሉ።

ዩናይትድ ኪንግደም ውስጥም በጥቂት ሳምንታት ውስጥ ተመሳሳይ መተግበሪያ ይፋ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል::

አዉሎ ሚዲያ ሚያዚያ 19/2012 ዓ.ም

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ