በአለም አቀፍ ደረጃ በኮቪድ-19 የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ200 ሺህ በላይ ሆነ

0
91

የጆህን ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ ሪፖርት እንደሚያሳየው በአለም አቀፍ ደረጃ በኮቪድ-19 ቫይረስ ምክንያት የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ200 ሺህ በላይ ሆኗል፡፡

በአለም አቀፍ ደረጃ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ2 ሚሊዮን 921 ሺህ በላይ ስለመሆኑም ተዘግቧል፡፡

ከቫይረሱ ጋር የተያያዙ ዝርዝር መረጃዎችን የሚለቀው የጆህን ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ ሪፖርት መሰረት ወረርሺኙ እስካሁን የ203 ሺህ 289 ሰዎች ሕይወት ቀጥፏል፡፡

ከዚህ ውስጥ ከ50 ሺህ በላይ የሚሆነው ሞት የተመዘገበው በቫይረሱ ክፉኛ እየተጎዳች በምትገኘው አሜሪካ ነው፡፡

ከአሜሪካ በመቀጠል ጣሊያን፣ስፔን፣ ፈረንሳይና እንግሊዝ እያንዳንዳቸው ከ20 ሺህ በላይ ሞት ያስመዘገቡ ሀገራት ሆነዋል ሲል ቢቢሲ አስንርብቧል።

አዉሎ ሚዲያ ሚያዚያ 18/2012 ዓ.ም

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ