በቻይና ውሃን ከተማ ሁሉም የኮሮና ቫይረስ ታማሚዎች አገግመው ከሆስፒታል መውጣታቸው ተነገረ

0
85

ለመጀመሪያ ጊዜ በኮሮና ቫይረስ የተያዘ ሰው በተገኘባት የቻይናዋ ከተማ ውሃን የሚገኙ የኮሮና ታማሚዎች በሙሉ ከሆስፒታል መውጣታቸውን ባለሥልጣናት አስታውቀዋል።

በፅኑ ህሙማን ማገገሚያ የነበሩት የመጨረሻው ታማሚ ከበሽታው አገግመው አርብ እለት ከሆስፒታል መውጣታቸውን የብሔራዊ ጤና ኮሚሽን ቃል አቀባይ ሚ ፌንግ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።

ቃል አቀባዩ በከተማዋ በቫይረሱ የተያዘ አዲስ ሰው እንደሌለም አክለዋል።

በቻይና ወረርሽኙ በታህሳስ ከጀመረ አንስቶ 82 ሺህ 816 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ 4 ሺህ 632 ሰዎች መሞታቸው ተነግሯል።

ከእዚህ መካከል 56 በመቶ የሚሆኑት ወይም 46 ሺህ 452ቱ የተመዘገቡት በውሃን ከተማ ነው ሲል የዘገበው ቢቢሲ ነው፡፡

አዉሎ ሚድያ ሚያዚያ 18/2012 ዓ.ም

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ