ሳዑዲ አረቢያ የኮሮናቫይረስን ለመግታት ጥላው የነበረ አስገዳጅ መመሪያ አላልታለች

0
84

ሳዑዲ አረቢያ የኮሮናቫይረስን ለመዛመት ጥላቸው የነበሩ አስገዳጅ መመሪያዎቿን አላልታለች።

ለ24 ሰአታት ተጥሎ የነበረው የሰአት እላፊ የሚነሳ ሲሆን ሰዎች ወጥተው መንቀሳቀስ ይችላሉም ተብሏል።

ከመጪው ረቡዕ ጀምሮ መገበያያ መደብሮች ይከፈታሉ፤ አንዳንድ ፋብሪካዎችም ስራ ይጀምራሉ።

ህጓን ያላላችው የረመዳንን ፆም በማስመልከት እንደሆነ ያሳወቀችው ሳዑዲ አረቢያ፤ አካላዊ ርቀትን ለመጠበቅ በሚያዳግቱ እንደ ጂምናዚየምና ሬስቶራንቶች ያሉ ቦታዎችን ግን አይመለከትም ብላለች።

ሙሉ በሙሉ ዝግ የሆኑት መካና መዲና በመሳሰሉ ከተሞቿ የተላለፉት መመሪያዎች የሚቀጥሉ ይሆናል፤ ቤት መቀመጥም አስገዳጅ እንደሆነ ይቀጥላል።

በሳዑዲ አረቢያ 16ሺህ ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን 136 ሰዎች ደግሞ ህይወታቸውን አጥተዋል።

አዉሎ ሚድያ ሚያዚያ 18/2012 ዓ.ም

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ