የአዉሮፓ ህብረት መሪዎች ኢኮኖሚያቸው ከውድቀት ለመታደግ በጋራ ለመስራት ተስማሙ

0
132

የአውሮፓ ሀገራት ከሁለተኛ የአለም ጦርነት በኋላ ማለትም ከ 50 ዓመታት በኋላ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ ኢኮኖሚያቸው ሊሽመደመድ ጫፍ ላይ ደርሷል፡፡

የአውሮፓ ሀገራት በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት አደጋ ላይ የነበረው የኢኮኖሚ እንቅስቃሲያቸው ለወራት ሊያገግም ባለመቻሉ ነው እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሱት ፡፡

የአውሮፓ ኮሚሽን ለኢኮኖሚ ማገገምያ ተብሎ 325 ቢሊዮን ዶላር  ፈንድ የበጀተ ሲሆን እንዲሁም ከካፒታል ገበያዎች ሌላ 350 ቢሊዮን ዶላር ብድር ለመውሰድም ሀሳብ አቅርቧል፡፡

በኮሮና ቫይረስ ምክንያት እጅጉን ከተጎዱ ሀገራት  ዋናዎቹ የአውሮፓ ህብረት ሀገራት ናቸው፡፡ ከዚህ በፊት የኢኮኖሚ ተሳትፏቸው ከፍተና የነበሩት ሀገራት በዚህ ቫይረስ ምክንያት ኢኮኖሚያችው ወደታች ስያሽቆለቁል የዜጎቻቸው የስራ አጥ ቁጥር ግን በፍጥነት አያሻቀበ የገኛል፡፡

በአውሮፓ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች  ቁጥሩ አያደገ ይገኛል፡፡ የአለም ጤና ድርጅት ትላንት በአውሮፓ ሀገራት የኮሮና ቫይረስ ከዚህ የከፋ አደጋ ሊፈጥር ይችላል ማለቱ ይታወሳል፡፡

አዉሎ ሚዲያ ሚያዚያ 16/2012 ዓ.ም

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ