የትግራይ በሄራዊ ክልላዊ መንግስት በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ላይ ማሻሻያ አደረገ

0
297

የትግራይ ክልላዊ መንግስት የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ለመከላከል ሲባል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጁ ይታወሳል፡፡

የክልከላዎቹ ዝርዝርም በክልሉ ህዝብ ግንኙነት በኩል ለህዝብ በይፋ ተደረጎ ለዚህ በተቋቋመ ግብረ ሀይል ክትትል ሲደረግባቸው መቆየቱ የክልል ህዝብ ግኑኝነት ቢሮ በፌስቡክ ገፁ አስነብቧል፡፡

በአስቸኳይ ግዜ አዋጁ ክልከላ ተደርጎባቸው የነበሩት ከፊሎቹ ማሻሻል መደረጉ ትላንት የክልሉ ምክትል ር/መስተዳደር ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል፡፡

 ማሻሻል የተደረገባቸውም  ቡና አፍልቶ የሚሸጡ ቡና ቤቶች፣ ካፌ ፣ ጁስ ቤቶች  እንዲሁም መጠጥ ቤቶች ናችው ብለዋል ር/መስተዳደሩ፡፡

የህ ተፈፃሚ ለማድርገም ርቀታቸው የጠበቁ መቀመጫ ወንበሮች እንዲሁም አስፈላጊ ኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሚረዱ መከላከያ ዘዴች ሁሉም መጠቀም የግድ ይላቸዋል ነው የተባለው፡፡ ይህ ሳይሆን ከቀረ ግን እንዲዘጉ ይደረጋል ተብሏል፡፡

አዉሎ ሚዲያ ሚያዚያ 16/2012 ዓ.ም

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ