ተቋርጦ የነበረው የጀርመኑ ቡንደስ ሊጋ የፊታችን ግንቦት ወር ሊጀመር ነው

0
176

በኮቪድ-19 ወረርሺኝ ምክንያት ለወራት ተቋርጦ የነበረው የጀርመን ቡንደስሊጋ ግንቦት አንድ ለማስጀመር ማቀዱን የጀርመን እግር ኳስ ሊግ አስታውቋል፡፡

በአለም አቀፍ ደረጃ የሊግ ጨዋታዎች እና ውድድሮች ለወራት የተቋረጡት የኮቪድ-19 ወረርሺኝ መስፋፋትን ተከትሎ ነው፡፡

ሀገሪቱ ቫይረሱን ለመከላከል ያደረገችው ጥረት ተስፋ ሰጪ መሆኑን ተከትሎ የተጀመሩ የሊግ ውድድሮች ፍፃሜያቸውን እንዲያገኙ እንደሚፈልግ ሊጉ አስታውቋል፡፡

የሀገሪቱ እግር ኳስ የበላይ ከመንግስት ፍቃድ የሚያገኙ ከሆነ ጨዋታዎችን ያለ ተመልካች ማካሄድ እንደሚጠበቅበት ተነግሯል፡፡

“ግንቦት ወር ውድድር ለመጀመር ዘግጅ ነን”ያሉት የጀርመን እግር ኳስ ሊግ ስራ አስፈፃሚ ክርስቲያን ሴፈርት ናቸው፡፡

የጀርመን መንግስት ቫይረሱን ለመቆጣጠር በሚል ብዙ ሰው የሚሰበሰብበት ሁነት እስከ ነሀሴ ወር መጨራሻ እንደማይኖር ማስታወቁ ይታወሳል፡፡

ምንጭ፡ቢቢሲ

አዉሎ ሚዲያ ሚያዚያ 16/2012 ዓ.ም

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ