በታንዛንያ ኮቪድ-19 ስርጭትን ለመከላከል እርምጃዎች በፍጥነት ባለመወሰዳቸው በርካታ ሰውን ለቫይረሱ አጋልጧል ተባለ

0
177

ታንዛንያ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ስርጭት ለመግታት ጠበቅ ያለ እርምጃ ባለመውሰዷ በአገሪቷ ከፍተኛ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ሊኖሩ ይችላሉ ሲል የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ።

የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ዳይሬክተር የሆኑት ማትስሺዲሶ ሞየቲ እንዳሉት ባለፉት ጥቂት ቀናት ውስጥ በምስራቅ አፍሪካ አገራት በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ሊጨምሩ ይችላሉ የሚል ስጋት አለ።

“በታንዛንያ አካላዊ ርቀትን መጠበቅ አለመቻሉ፣ ሕዝባዊ ስብሰባዎች አለመከልከላቸውና ጠበቅ ያለ ርምጃ ለመውሰድ በመዘግየቱ በአገሪቱ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎችን ቁጥር ከፍ ሊያደርገው ይችላል ብለን እናምናለን” ብለዋል በነበራቸው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ።

የታንዛንያው ፕሬዝዳንት ጆን ማጉፉሊ የኮሮናቫይረስን ስርጭት ለመግታት ጠበቅ ያሉ እርምጃዎችን ከመውሰድ ይልቅ ሕዝባቸው በእምነት ተቋማት እንዲሰባሰብ በመፍቀዳቸው በሰፊው ይተቻሉ።

ታንዛንያ በኮሮናቫይረስ የተያዘ የመጀመሪያውን ሰው ያገኘችው ከአንድ ወር በፊት ሲሆን እስከ ትናንት ድረስ 284 ሰዎች ቫይረሱ እንዳለባቸው ተረጋግጧል።

በታንዛንያ ትምህርት ቤቶች ለአንደ ወር ተዘግተው የነበሩ ሲሆን ይህም ለአንድ ሳምንት ተራዝሟል።

አዉሎ ሚዲያ ሚያዚያ 16/2012 ዓ.ም

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ