አምራች ኢንዱስትሪዎች ሰራተኞቻቸውን እንዳይበትኑ፣ምርታቸውንም እንዳያቆሙ ድጋፍ ሊደረግላቸው ነው

0
102

ለትላልቅ፣አነስተኛና መካከለኛ ኢንዱ ስትሪዎች ሰራተኞቻቸውን እንዳይበትኑ፣ ምርታቸውን እንዳይቀንሱና እንዳያቆሙ ድጋፍ የሚደረግላቸው መሆኑን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ ፡፡

የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል ትናንት በቢሮቸው በሰጡት መግለጫ እንዳመለከቱት፤ ትላልቅ፣አነስተኛና መካከለኛ ኢንዱስትሪዎች ሰራተኞቻ ቸውን እንዳይበትኑ፣ ምርታቸውን እንዳይቀንሱና እንዳያቆሙ ድጋፍ ያደርጋል ።

ቀደም ሲልም መንግስት አምራች ኢንዱስትሪዎችንና ኢንቨስትመንቱን ለማነቃቃት ለባንኮችን 15 ቢሊዮን ብር ፈሰስ አድርጓል፡፡ ይህም አምራች ኢንዱስትሪው ሊያጋጥመው የሚችለውን የስራ ማስኬጃ የገንዘብ እጥረት ለመፍታት ትልቅ አስተዋጽኦ አለው፡፡

የኮሮና ቫይረስ ተከትሎ በተፈጠረው የኢኮኖሚ መቀዛቀዝ ኢንዱስትሪዎች ሰራተኛ እንዳያሰናብቱ ፣ምርት እንዳይቀንሱ፣ ፋብሪካዎቻቸውን እንዳይዘጉ የተለያዩ ግብር ኃይሎች ተቋቁመው በቀጣይ የችግሩ ሁኔታ እየታየ ድጋፎች እንዲደረጉ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑንም ጠቁመዋል ፡፡

በተለይ ወቅቱ ካመጣው ችግር ጋር ተያይዞ የሚፈለጉ ምርቶችን እንዲያመርቱ የውጭ ምንዛሬ አቅርቦቱን የማሻሻል ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡ለአብነትም የሳሙናና ዲተርጀት ፋብሪካዎች ያለባቸውን የጥሬ ዕቃ ችግር በመፍታት በአጭር ጊዜ ፍላጎቱን በአገር ውስጥ ምርት ለመሸፈን 100ሚሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሪ በባንኮች በኩል ተመቻችቶላቸዋል ብለዋል፡፡

በኢትዮጵያ 18ሺ 855 በላይ አነስተኛና መካከለኛ ኢንዱስትሪዎች መኖራቸውን ጠቅሰው፤ እነዚህ ኢንተርፕራይዞች ወርርሽኙን ተከትሎ የገበያ መቀዛቀዝ እንዳያጋጥማቸውና በቀላሉ ከገበያ እንዳይወጡ ሚኒስቴሩ የድጋፍ ማዕቀፎችን ማዘጋጀቱን እና ችግሩን ሊፈቱ የሚችሉ ተቋማት ምላሽ እንዲሰጡ የችግር መውጫ ስትራቴጂ ተዘጋጅቶ ማቅረቡን ተናግረዋል፡፡

የድጋፍ ጥያቄው በሚመለከታቸው ተቋማት በአጭር ጊዜ ምላሽ ሲያገኙም ድርጅቶቹ ሰራተኞቻቻውን ሳይበትኑ ምርታቸውን እያመረቱ የሚቀጥሉና ለአገር ውስጥ ፍጆታዎች የሚውሉ ምርቶችን የሚያመርቱበት ሁኔታ እንደሚፈጠር አብራርተዋል፡፡

የወርሽኙ መከሰት ተከትሎ ከመጋቢት ወር በኋላ ሳኒታይዘርና የንጸህና መጠበቂያዎችን አቅርቦት ማሳደግ አስፈላጊ በመሆኑ በአገር ውስጥ ኢንዱስትሪዎች ከሶስት ሚሊዮን ሊትር በላይ ሳንታይዘር ተመርቶ ለገበያ እንዲቀርብ መደረጉን ያመለከቱት አቶ መላኩ፤ 207 ሚሊዮን ሊትር ኢታኖል ተመርቶ ሳኒታይዘር ለሚያመርቱ ፋብሪካዎች ተሰራጭቷል ብለዋል፡፡

አዉሎ ሚድያ ሚያዚያ 15/2012 ዓ.ም

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ