የነገዋ አለም!!

0
341

በሀገር ተ/ብርሀን

ኮሮና ቫይረስ በዋናነት የሰው ልጅ ጤና እንደሚያቃውስ የሚታወቅ ቢሆንም ፣ የሰው ልጅ ለመኖሩ ዋስትና ከሆነው አንዱ ቁጠባ (ኢኮኖሚ) ማሽመድመዱ አልቀረለትም። ከቀን ወደቀን ሁኔታዎች እየተቀየሩ ናቸው ፣ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የተነሳ ዓለማችን ክፉኛ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎቿ ተመተው ከ10 አመት ቡኋላ አለማችን ከባድ የኢኮኖሚ ድቀት ያጋጥማታልም ይላሉ የዘርፉ ሙሁራን።

ኮቪድ 19 ኮሮና ቫይረስ በቻይና ከተቀሰቀሰበት ጊዜ ጀምሮ ብሎም አለማቀፍ ወረርሽኝ ተበሎ ከታወጀ ቡኋላም አለማቀፍ የኢኮኖሚ ትስስሮች ከባድ ተፅእኖ ውስጥ ናቸው ፤ እንዲሁም ከ ሀገር ሀገር የሚዘዋወሩ ምርቶች እንቅስቃሴያቸው ተገቷል። በኢኮኖሚ ጉዳይ ለሚፈጠሩ ሁኔታዎች የሚተነትኑ ሊሂቃን በአንድ ጉዳይ ላይ ይስማማሉ “ከዚህ በፊት በቻይና እና አሜሪካ ተቀስቅሶ የነበረውን የንግድ ጦርነት ምንም እንኳን የነሱ ጦርነት ባላደጉ ሀገራት ሄዶ የሚፈነዳ ጦር ቢሆንም በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ግን ይህ የሚቀየርበት ብሎም አዲስ የኢኮኖሚ ዘውግ ተፈጥሮ ሌሎች አለማቀፍ የኢኮኖሚ ትስስሮች ይፈጠራሉ” ይላሉ ።

ዓለማችን ኮቪድ19 ኮሮና ቫይረስ ከመከሰቱም በፊት ቢሆን በተከታታይ የምርት እድገቷ እያሽቆለቆለ መጥቷል። እንደ UNIDO ሪፖርት በ2019 እ.ኤ.አ አራተኛ ሩብ አመት የምርት እድገት ከ1% ዝቅ ብሎም 0.7% ድረሷል።

የአውሮፓ ሀገራት በተለይ ኢንግላንድ ሳምንቱ በወጣው ሪፖርት እንኳን ብንመለከት በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የተነሳ 2 ሚሊዮን የሚሆኑ ዜጎቿ ስራጥ ይሆናሉ፤ እንዲሁም ከ300 አመት ብኋላ እይታው የማታቀው የኢኮኖሚ ቀውስ ያጋጥማታልም እየተባለ ነው።

ልእለ ሀያሏ ሀገር  ፣ያቺ ድንበር የማይበግራት ፣ያቺ ስንቱን አልማ ተኩሳ የጣለች ሀገር አሜሪካ ኮሮና ቫይረስ ግን ተኩሳ መጣል ፣ በማእቀብ ማስቆም አልቻለችም ። በአመታዊ በጀቷ ሳይቀር ጭማሪ ያስፈልገኛል ማለቷ ይታወሳል።

በቅርቡ እንኳን 6.65 ሚሊዮን ዜጎችዋ ስራ የለንም ሲሉ በቀረበላቸው የመጠይቅ ወረቀት ላይ አስፍሯል።

በ2019 4ተኛ ሩብ አመት ማለትም በ2019 መገባደጃ ማለት ነው 3 የኢንዲስትሪ ዘርፎች ብቻ  ወጤታማ ነበሩ። እነሱም ህክምና(መድሀኒት) ኢንዳስትሪ፣ የመጠጥ እንዲሁም  የምግብ እንዳስትሪ ብቻ ነበሩ፡፡

በርግጥ እነዚህ የኢንዳስትሪ ዘርፎች እጅግ ወሳኝ እና አስፈላጊ መሆናቸው የማይካድ ሀቅ ቢሆንም ሌሎች ኢኮኖሚው ተሸክመው የነበሩት ኢንዲስትሪዎች ቀድመዉንም ከአሜሪካና ቻይና የንግድ ጦርነት ጋር በተያያዘ ሲንገዳገዱ የነበሩ ከመሆናቸው አንፃር የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ታክሎበት እንዲሽመደመዱ ሆነዋል። እንደ  IMF እና WEO ትንበያ ከሆነ በቀጣይ ወራት አለም ኢኮኖሚዋ ክፉኛ ይመታል እድገቷም እንዳያሽቆለቁል ያስፈራል የሚል ሪፖርት እያስነበቡን ይገኛሉ።

በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ሶስቱ የአለማቀፍ ኢኮኖሚ መስመሮች ማለትም ተጠቃሚነት(ፍላጎት) ፣ አቀርቦት እንዲሁም ፋይናንስ እክል ሊደርሳችው ይችላል ተብሎ ይጠበቃል።

በፍሎጎት አንፃር ሆነን ብንመለከት እንኳን ሰዎች በቫይረሱ መስፋፋት የተነሳ እንደ ከዚበፊቱ ሲራ ወጥተው መግባት ስለሚአዳግታቸው ገቢያቸውም በዚያው ልክ ማሽቆልቆልሉ አይቀሬ ነው፤ የሰው ልጅ ፍላጎት ከገቢው አንፃር የምሆኑ እድል ሰፊ ስለሆነ የመሸመት አቅሙ፣የመፈለግ አዝማኢያሚያው ይኮላሻል። ይህ ሄዶሄዶ መንግስትን ጫና ውስጥ ማስገባቱ የማይቀር ይሆናል።

ስለ አቅርቦት ያወራን እንደሆን ፣ አቅርቦት ከፍላጎት ጋር እጅጉን የተቆራኘ ትስስር አለው። የሚፈልግ ማህበረሰብ፣ መሸመት የሚችል ሽማች ሲኖር ነው አቅርቦቱም በዛው ልክ የዋጋ ፉክክር ታክሎበት ወደ ገበያ የሚወጣውና። በተጨማሪ ኮሮና ቫየረስ በአቅርቦት አንፃር የኢኮኖሚ ሚዛን ማዛባት እያደረሰ ይገኛል።

ለመሳሌ የተለያዩ ፋብሪካዎች መደበኛ ስራቸውን በማስቆም ወደ አንድ ምርት ማምረት ተሸጋግረዋል፤ የተለያይ መጠጦች በማምረት ኢኮኖሚውን የሚያሽከረክሩ ፋብሪካዎች አሁን አልኮል ብቻ በማምረት ሊጠመዱ ይችላሉ ፣ የጨርቃጨርቅ ፋብሪካዎች የምርት አይነታቸው አንድ እንዲሆን እያደረገ ይገኛል። እንዲህ እንዲህ እያልን የኦኮኖሚ ሚዛን የሚያአስጠብቁ ኢንድስትሪዎች አሁን ገበያ ላይ ባለመኖራቸው ምንያህል ኢኮኖሚው እንደሚንገዳገድ መገመት አይከብድም።

ስለ ፋይናንስ ፤ፋይናስ ስንል ብር መሆኑ ነው። እነዛ ከላይ የተጠቀሱት የኢኮኖሚ መስመሮች ሄደው ሄደው ማሰሪያቸው ፋይናንስ(ብር) ነው። በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በአለም ደረጃ የፋይናንስ (ብር) እንቅስቃሴው እግሩን ታስሮ እጁ እያወራጨ እንደሚዘል ሰው ፣ መሄዱን አላቆመም ግን ደግሞ ቢሄድ የትም የማይደርስ ኢኮኖሚ ሁንዋል።

ሌላው በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የአለማቀፉ ኢኮኖሚ መንገራገጭ ተከትሎ የተለያዩ ባንኮች የምጥ ያህል እየተጨንቁም ነው። ይህ የአለማቀፍ ኢኮኖሚ መንገዳገድ ተከትሎ የአልማቀፍ የብር ምንዛሬ አንዴ ከፍ አንዴ ዝቅ እያል ሊዋዥቅም ይችላል። እንዲሁም ስራ አጥ በገፍ መብዛቱ አይቀርም።

ይህ ቫይረስ በእድሜ የገፉትን ሰዎች የሚያጠቃውን ያህል ወጣቶችም ማጥቃቱ አይቀርም። ምክንያቱም በዚህ ወረሽኝ የተነሳ ብዙ ወጣት ስራ አጥ የሚሆንበት እድል ሰፊ ነው።

 ሀገራችን ኢትዮጵያም የዚህ ገፈጥቀ ማሽ ከሆኑት ሀገራት አነዷ እና ዋነኛዋ ናት። ቀድሞውንም ኢኮኖሚዋ በሁለት እግሩ ያልረገጠው ፣በተለይ ከ2 አመት ቡኋላ የሀሪቷ ኢኮኖሚ ሊቆምበት የነበረው ምሰሶ ፈራርሶ ሌላ የአለም ባንክ የቸረንን የኢኮኖሚ ፖሊሲ ለመከተል በምንሯጥበት ጊዜ ይህ መከሰቱ ጉዳዩ ከባድ ያረገዋለ።

በኢትዮጰያ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በትልልቅ ተቋሞችዋ ብሎም እስከታች ተራ ሸማቾች የከፋ የኢኮኖሚ ቀውስ ከማድረሱ በፊት መንግስት የተለያዩ ማስተካካያዎች መውሰድ አለበት ይላልሉ የዘርፉ ሊህቃን። የኢትዮጵያ አየር መንግድ እንኳን ኮሮና ቫይረስ ከተከሰተ ቡሃላ ከግማሽ ቢሊዮን ዶላር በላይ ግቢዬ ቀንስዋል ሲል ሪፖርት አድርጓ ፤ እንዲሁም በሃገር ውስጥ ያልው የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ እየተገታ የመጣበት ሁኔታ ነው ያለው። የዚህ ማሳያ ከከተማ ከተማ የህዝብ እንቅስቃሴ ወረርሽኙ ለመግታት ሲባል እንዲቆም ቢባልም በዛው ልክም ገበያው ይዞት መቆሙ የማይቀር ነው።

ከሰሞኑ የተለያዩ የኢኮኖሚ ሙሁራን ባንኮች ይወለድ ማሻሻያ በማድረግ ኢኮኖሚው መታደግ አልያም ማስታመም  ይቻላል ሲሉ ምክረ ሀሳብ  እየሰጡ ነው ።

መንግስታችንስ ከግዚያዊ በዜና ከመንሰማቸው የተለያዩ ድጋፎች ውጪ ሌላ ኢኮኖሚያችን እንዳይድቆስ ያሰበው መላ ፣ያሰበው ግዚያዊ መፍትሄ ይኖር ይሆን?

ቸር ያሰማን!!!!

አዉሎ ሚዲያ ሚያዚያ 08/2012 ዓ.ም

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ