በርካታ ኬንያውያን ከለይቶ ማቆያ ሊያመልጡ መሞከራቸው ተሰማ

0
89

ቁጥራቸው በርከት ያሉ ኬንያውያን መንግስት ካዘጋጀው የለይቶ ማቆያ ማዕከል ውስጥ ለማምለጥ መሞከራቸው ተሰምቷል።

በማቆያው ቦታ ያለው ሁኔታ እጅግድ ከባድ ነው ስለዚህ እዚህ መሆን አንፈልግም ሲሉ ነው ኬንያዊያኑ ከለይቶ ማቆያው ሊያመልጡ የሞከሩት ተብሏል፡፡

ኬንያ ድንበሮቿን ከመዝጋቷ በፊት ወደ አገሪቱ የገቡ ሰዎች በለይቶ ማቆያዎች ውስጥ እንዲገቡ ተደርገው እንደነበር ቢቢሲ ነው ያስነበበው።

ነገር ግን መንግስት ያስቀመጠውን የጊዜ ገደብ ቢጨርሱም ለተጨማሪ ቀናት በለይቶ ማቆያ ውስጥ እንዲቆዩ መደረጋቸውን ዘገባው አስታውሷል።

“ከዚህ በኋላ ወደ ማዕከሉ የመመለስ ፍላጎት የለንም። አንደኛ ሳይንሱ ለሚያዛቸው ቀናት ያክል በለይቶ ማቆያው ቆይተናል፤ ሁለተኛ ከዚህ በላይ ለመንግስት መክፈል አንችልም‘’ ብሏል በኬንያታ ዩኒቨርሲቲ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለው ሲሞን ሙጋምቢ።

“ሁለት ጊዜ ተመርምረን ውጤታችን ቫይረሱ እንደሌለብን ቢያሳይም በለይቶ ማቆያው እንደንቆይ ተደርገናል” ማለታቸውን ቢቢሲ በዘገባው አስፍሯል።

በኬንያ አጠቃላይ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች 225 ሲሆኑ 10 ያህሉት ሰዎች ደግሞ ለህልፈተ ህይወት ዳርጓል።

አዉሎ ሚዲያ ሚያዚያ 08/2012 ዓ.ም

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ