አሜሪካ ለዓለም ጤና ድርጅት የማዋጣውን ገንዘብ አቋርጫለሁ አለች

0
98
Mandatory Credit: Photo by Evan Vucci/AP/Shutterstock (10434333bm) Donald Trump, Sauli Niinisto. President Donald Trump speaks during a meeting with Finnish President Sauli Niinisto in the Oval Office of the White House, in Washington Trump, Washington, USA - 02 Oct 2019

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለኮሮናቫይረስ የሰጠው ምላሽ ቀርፋፋ ነው፤ በአካሄዱም ቻይናን ማዕከል አድርጓል ላሉት የዓለም ጤና ድርጅት አገራቸው የምታበረክተውን የገንዘብ መዋጮ እዲቋረጥ አዘዋል።

ይህም ማለት አሜሪካ ለድርጅቱ በየዓመቱ ለድርጅቱ ትሰጥ የነበረው ገንዘብ እንዲቆም የሚያደርግ ነውም ተብሏል።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ የትራምፕን ውሳኔ “ጊዜውን ያላገናዘበ እርምጃ” ሲሉ ተችተውታል።

ዶናልድ ትራምፕ ከሳምንታት በፊት ዶ/ር ቴድሮስ አድኃኖም የሚመሩትን መሥሪያ ቤት ክፉኛ ሲወቅሱ ነበር። በየዓመቱ የሚሰጡትን መዋጮ ለማጤን እንደሚገደዱም መጠቆማቸው ይታወሳል።

አዉሎ ሚዲያ ሚያዚያ 07/2012 ዓ.ም

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ