አሮጌ ጫማ ለማደስ በተከራዩት ቤት ውስጥ 1 መትረየስ እና 7 ክላሽ ጠመንጃ ሸሽገው የተገኙ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

0
263

የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አሮጌ ጫማ ለማደስ በተከራዩት ቤት ውስጥ አንድ መትረየስ እና ሰባት ክላሽን-ኮቭ ጠመንጃ ሸሽገው የተገኙ ሁለት ተጠርጣሪዎችን ይዞ ምርመራ እያጣራ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

ፖሊስ የመሳሪያውን ምንጭ እና ለምን ተግባር ሊውል እንደ ነበር ለማወቅ ምርመራውን መቀጠሉን የክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ የወንጀል እና ትራፊክ አደጋ ምርመራ ዲቪዚዮን ኃላፊ ኮማንደር ጌታነህ በቀለ ገልፀዋል፡፡

ተጠርጣሪዎቹ ፍ/ቤት ቀርበው የጊዜ ቀጠሮ ተጠይቆባቸው በማረፊያ ቤት እንደሚገኙ ተገልጿል፡፡ አዲስ በፀደቀው የጦር መሳሪያ አዋጅ ሕገ-ወጥ የጦር መሳሪያ ማዘዋወር ሆነ ይዞ መገኘት የሚስከትለው ቅጣት ከፍተኛ መሆኑ ወንጀሉን ለመከላከል የራሱ ጠቀሜታ ይኖረዋል ተብሏል፡፡ ዘገባው የ ኢቢሲ ነው።


አዉሎ ሚድያ ሚያዚያ 02/2012 ዓ.ም

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ