የትዊተር ባለቤት የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል የአንድ ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ ሊያደርግ ነው

0
88

የትዊተርና የመገበያያ መተግበሪያው ሶፍትዌር መስራች ጃክ ዶርሴ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት ለመደገፍ የ1 ቢሊየን ዶላን ድጋፍ እንደሚያደርግ በትዊተር ገፁ ይፋ አድርጓል። የትዊተርና የስኩዌር የበላይ ኃላፊ የ43 ዓመቱ ጃክ ዶርሴ ድጋፉ የሀብቱን 28 በመቶ እንደሚሆንም አስታውቋል።


ባለሀብቱ ዶርሴ ኮቪድ 19 ለመዋጋት የሚውለው ድጋፍ ለማን እንደሚላክ በግልጽ አላስቀመጠም ተብሏል፡፡ በአሜሪካ የመተንፈሻ ማሺኖች እንዲሁም የሕክምና ባለሙያዎች የሚያደርጉት መከላከያ አልባሳት እጥረት ያለ ሲሆን በንግድ ሥራ ላይ የተሰማሩ እና ግለሰቦችም በገቢ ማጣትና መቀዛቀዝ ክፉኛ ተጎድተዋል ተብሏል።


ጃክ ዶርሲ እንዳለው ስኩዌርር የተሰኘው መተግበሪያ ላይ ያለውን ድርሻ የሚጠቀም ሲሆን ለዚህም በምክንያትነት ያስቀመጠው ከትዊተር ይልቅ ከፍ ያለ የአክስዮን ድርሻ ባለቤት የሆነው ስኩዌር መተግበሪያ ላይ መሆኑን ነው።

በጊዜ ሂደት አክሲዮኖቹ ተሽጠው ለበጎ አድራጎት ተግባሩ የሚውሉ ይሆናል። የኮቪድ-19 በቁጥጥር ሥር ከዋለ በኋላ ደግሞ ፈንዱ ለሴቶች ጤናና ትምህርት እንዲሁም ለመሰረታዊ ገቢ ጥናት የሚለገስ ይሆናል።
የፌስ ቡክ መስራች ማርክ ዙከርበርግ 30 ሚሊዮን ዶላር ለመስጠት ለወረርሽኙ የሚደረገውን ህክምና ለማገዝ ቃል መግባቱም ተነግሯል።


የአማዞኑ ጄፍ ቤዞስ በበኩሉ 100 ሚሊየን ዶላር በመስጠት በዚህ ወቅት በአሜሪካ በምግብ እጥረት ለሚቸገሩት ለማገዝ እንዲውል ብሏል። የአፕል ባለቤት ቲም ኩክ ደግሞ በኮሮናቫይረስ ክፉኛ ለተጎዳችው ጣሊያን የሕክምና ቁሳቁስ ድጋፍ እንደሚያደርግ ያስታወቀው ባለፈው ወር እንደነበር ቢቢሲ አስነብቧል።


አውሎ ሚድያ መጋቢት 30/2012 ዓ.ም

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ