ታክሲዎች የመጫን አቅማቸው በግማሽ እንዲቀንስ እና ተሳፋሪዎችም ዕጥፍ እንዲከፍሉ ተወሰነ

0
281

በአዲስ አበባ አገልግሎት የሚሰጡ ታክሲዎች የሰው መቀራረብን ለመቀነስ የመጫን አቅማቸው ግማሽ ብቻ እንዲጭኑ መባላቸው ይታወሳል፡፡

ታድያ ዛሬ ከከቲባው ፅ/ቤት የወጣው መረጃ እንደሚያሳየው ውሳኔው ተሳፋሪዎች ደረስ የሚዘልቅ ሁንዋል ፣ ማለትም ተሳፋሪዎች ከዚህ በፊት ከሚከፍሉት የየትኛውም ርቀት ታሪፍ ዋጋ እጥፍ እንዲከፍሉ ነው የተወሰነው፡፡

የአንበሳ አውቶብስና ሸገር አውቶብስ ደግሞ ያለምንም የዋጋ ጭማሪ 30 ሰው ብቻ እንዲጭኑ ተወስኗል፡፡

ውሳኔው ከነገ ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆን ሲሆን ከሰዓታት በኃላ በዚህ ጉዳይ ዙሪያ ዝርዝር መረጃዎች የሚሰጡ ይሆናል መባሉን ከከንቲባ ጽህፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያሳያል፡፡

አዉሎ ሚድያ መጋቢት 28/2012 ዓ.ም

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ